‹ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል ከሃገር ውጭ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

July 29, 2014

ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል ከሃገር ውጭ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ
– ዛሬ ማታ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ይጠበቃል
የማይገባቸውን የትምህርት ደረጃና ማዕረግ ለራሳቸው ሰጥተው ያለአግባብ ጥቅም ሲያገኙ ቆይተዋል በሚል ሲብጠለጠሉ የቆዩት ‹ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል በሚገኙበት ኬንያ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉና ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡
ግለሰቡ አደረጉት የተባለው ጉዳይ በመገናኛ ብዙሃንና በማኅበራዊ ድረገፆች ከተነሳ በኋላ በተለያየ መንገድ ገንዘብ ተጭበርብረናል ያሉ ሰዎች ክሳቸውን አቅርበው ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል መረጃዎቹ መነገር ከጀመሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ኬንያ ተጉዘው የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስ የኢንተርፖል ቡድን እና ከኬንያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ከቀናት በፊት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርጓል፡፡
የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች እንደገለፁት ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ወደ ሃገር ቤት የሚመጡበት ሂደት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የተጠርጣሪውን ጉዳይ ለማስፈፀምና ወደ አዲስ አበባ ይዞ ለመምጣትም አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር አባል ወደ ናይሮቢ እንደሄዱ ተነግሯል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s