የአቶ ሃ/ማርያም ደህንነት

ከኢየሩሳሌም አረአያ

እያብ ምህረተአብ ይባላል፤ ኤርትራዊው እያብ በ1968 ዓ.ም ሕወሐት እንደተቀላቀለ ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ከ6ኛ ክፍል ያቋረጠውን ትምህርት አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ሲቪል ሰርቪስ ተምሮ “ተመረቀ” ተባለ። የሜጋ ፎቶግራፍ ሆኖ ተመደበ። ህንድ አገር ሄዶ ተማረ ከተባለ በኋላ ሲመለስ ስብሃት ነጋ የኤፈርት ሃላፊ በነበሩበት ወቅት አማካሪ ዴክስ ተደርጎ ተሾመ። አቶ ሳሙኤል ገ/ዋህድ የተባለ የጠ/ሚ/ር መለስ አማካሪ በ1996ዓ.ም በኢሮብ ህዝብ በጥይት ተደብድቦ ከተገደለ በኋላ በቦታው እያብ ተሾመ። በ2002 ምርጫ ሃይለማርያም ደሳለኝ ም/ል ጠ/ሚ/ር ተደርገው ሲሾሙ እያብ ደግሞ በመለስ ዜናዊ የጠ/ሚ/ር ረዳት (አማካሪ) በሚል ሽፋን ተመደበ። እያብ የተሾመው የሃ/ማርያምን እንቅስቃሴ እግር በግር እንዲከታተል በመለስ ደህንነት ተደርጐ መመደቡን ምንጮቹ ያመለክታሉ።

የእያብ እህት ወ/ሮ ሂሩት ምህርተአብ ትባላለች፤ ሂሩት የአባዲ ዘሞ ባለቤት ስትሆን የትግራይ ክልል ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ናት። መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ እያብ የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ልዩ አማካሪ ተብሎ በነደብረፂዮን የተመደበ ሲሆን ሃ/ማርያምን የሚዘውረው እያብ ነው። ከህወሀት ባለስልጣናት ተወስነው የሚመጡ ማናቸውም ጉዳዮች ሃ/ማርያም እንዲፈርሙ የሚደረገው በእያብ መሆኑን ምንጮቹ ያረጋግጣሉ። የጋምቤላ የቀድሞ ፕ/ትና የአንዳርጋቸው መያዝ እንዲሁም የተቃዋሚ አመራሮችና ጋዜጠኞች ወዘተ..እስርና አፈና ውሳኔ በሕወሐት ሹማምንት ከተወሰነ በኋላ ለፊርማ ሃ/ማርያም ዘንድ የሚመጣው በእያብ በኩል ነው። 12ቱ ወሳኞችን በተመለከተ እመልስበታለሁ።

Ze-Habesha

posted by Gheremew Araghaw

Advertisements

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየወጡ ያሉ ስሞች

1. ልማቱ ፈጠነ
2. ቦንድነህ አባይ
3. ሊግ ይበልጣል
4. አኬልዳማ ታዬ
5. ኑሮ ውድነህ
6. ፌደራል እርገጤ
7. ስልጣኑ በዛብህ
8. ኮንዶሚኒየም ለማ
9. ግምገማ ከበደ
10. ተሳለጭ ሃገሬ
11. መተካካት ተሻለ
12. ባድመ ይበቃል
13. አሰብ ተስፋዬ
14. ቻይና ፍቅሩ
15. መብራት ይታገሱ
16. ቴሌነሽ በዝብዝ
17. አክስዮን ሰብስቤ
18. ቫቱ በዛብህ
19. ግብሩ ጫንያለው
20. ህገመንግስት ጣሴ
21. ነጠፈ ብሩ
22. ፌስቡክ ተመስገን
23. ሀያልነሽ መንግስቴ
24. አምስትለአንድ አደራጀው
25. ግንቦት ሃያ ገብረማርያም

(ምንጭ: Ethio-Sunshine ፌስቡክ)

በአንባቢያን የተጨመሩ:

Gulilat Kasahun የጨመሩት

1. ምርጫዬ ደረሰ
2. ደሞዝ ስሜነህ
3. ይበቃል ገዛኸኝ
4. ብርቅይሁን ምሳዬ
5.ሞላልኝ ጎርፉ
6. ብሩ ባይከዳኝ

– See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1496#sthash.xxmi0365.LTw0OTQ1.dpuf

በአዲስአበባ የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት መዳከም አሳሳቢ ሆኗል

የኢትዮ- ቴሌኮም በአዲስአበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማሳደግ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ
ደርሻለሁ ቢልም የአገልግሎቱ ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እየወደቀ መምጣቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ምሬት ውስጥ እየከተተ ነው፡፡

በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ወጪ የቻይናዎቹ ሁዋዌ እና ዜድቲኢ የሚባሉ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያውን ፕሮጀክት ለመስራት ከኢትዮቴሎኮም ጋር በዚህ ዓመት መጀመሪያ የተፈራረሙ ሲሆን የአዲስአበባው ፕሮጀክት እስከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ነበር፡፡ ኢትዮቴሌኮም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በስኬት ተጠናቋል በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሞባይል ሒሳብ ለመሙላትና ቀሪ ሒሳብ ለመጠየቅ አለመቻል፣ የፈለጉትን ሰው በቀላሉ ደውሎ ማግኘት አለመቻል፣ ያልደወሉበት ሒሳብ መቆረጥ፣ የሞባይል ኢንተርኔት በተለይ ፈጣን ነው የተባለውን 3ጂ ጨምሮ ደካማ መሆን፣ የፌስቡክ አካውንት አለመከፈት፣ የገመድ አልባ ኢንተርኔትና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥና ደካማ መሆን በስፋት እየታየ ነው፡፡

ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች የአፍሪካ ህብረትና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሆነችው አዲስአበባ ጥራት ያለው የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት ብርቋ መሆኑ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ እንዳሉት ኢትዮቴሌኮም የተሻለ ማስፋፊያ አድርጌለሁ እያለ በተግባር ይህ አለመታየቱ ምናልባትም መንግሥት በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች እየተሰነዘረበት ያለውን ጠንካራ ተቃውሞና ትችት ለማፈን የተጠቀመበት አዲስ ዘዴ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንደገባው ተናግሮአል፡፡

የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደመብራት ብልጭ ድርግም እያለ ብዙዎች በመበሳጨት አገልግሎቱን እየተው ነው ያለው አስተያየት ሰጪያችን መንግሥት በዚህ ሒደት ከሚያጣው ገንዘብ ይልቅ ተቃዋሚዎቹን ለማፈን ትልቅ ግምት ሳይሰጠው እንዳልቀረ አስረድቷል፡፡

posted by Aseged Tamene

ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ፈተናዎች ተብለው ቀርበዋል

ነገረ-ኢትዮጵያ

በኢህአዴግ ጽ/ቤትና በትምህርት ሚኒስትር ትብብር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ አጀንዳ መሆናቸውን ሰልጣኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ›› በሚለውና በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ውጭ በየክልሉ እየሰለጠኑ ለሚገኙት ተማሪዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና ሰማያዊ ፓርቲና ቴዲ አፍሮ ለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ፈተናዎች ተብለው ቀርበዋል፡፡

አሰልጣኞቹ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹መንግስት የእምነት ነጻነት ያክብር!›› እያለ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በአክራሪነት የፈረጀ ሲሆን ቴዲ አፍሮም ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ለህዝብ ያደረሰው አልበም ተመሳሳይ ውንጀላ ቆርቦበታል ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊና ቴዲ አፍሮ በተለይ በውይይት ወቅት ከአሰልጣኞቹ ሰፋ ያለ ወቀሳና ውንጀላ እንደደረሰባቸው ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አንድ ለህዝብ እንደቆመ ፓርቲ መንግስት በእምነት ጣልቃ እንዳይገባ መጠየቅና መታገል መብቱ ብቻ ሳይሆን ግዴታው ነው፡፡›› ብለው እንደተከራከሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቁር ሰው አልበም በስልጠና ሰነዱ ላይ ለአክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ቴዲ አፍሮ ለአገር አንድነት የቆመ መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን ገልጸውልናል፡፡ ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹ጥቁር ሰው የሚለው ተወዳጅ ዘፈን በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ስር ከሚገኙት ውጭ በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች በስፋት ይለቀቃል፡፡ በስልጠናው እያየነው እንዳለነው ግን ገዥው ፓርቲ ቴዲ አፍሮን ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹንም በአክራሪነት እየከሰሰ መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በሰነዱ ‹‹ጠባብና ትምክተኛ ተብለው የተፈረጁ ኃይሎች ተመጋጋቢ ናቸው›› ተብለው የቀረቡ ሲሆን ‹‹የትምክት አስተሳሰብ የተጠናወተው ሚዲያ ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚል ዘፈን ሚኒሊክን ሲያሞካሽ በጠባብነት የተለከፈው ሚዲያ የአኖሌን ግፍ ህዝብን ለመለያየት ይጠቀምበታል›› ሲል ሁለቱንም በጅምላ ይወቅሳል፡፡ ይህን ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ‹‹ኢህአዴግ ራሱ በአኖሌ ስም እየነገደ ለእሱ የሚቀርቡት አካላት ከእነ ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ ፓርቲ ጋር አላትሞ መውቀሱ የሚያስገርምና ውይይት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ‹‹እራሱ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች ህዝብን እየነጣጠለና የከፋፍለህ ግዛ ስርዓት አስፍኖ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑትን አካላት በማይገባቸው ክስ መክሰሱ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች አላዋቂ አድርጎ መውሰዱንና ንቀቱን የሚያሳይ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

ሰልጣኝ ተማሪዎች የላኩልንን የሰነዱን አካል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡

የጋዜጣ አዙዋሪዎች ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አስታወቁ

በቅርቡ መንግስት በፋክት፣ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ፍትህ ሚኒስትር ክስ መመስረቱን ተከትሎ ሚዲያዎቹ ከህትመት በመውጣታቸው ምክንያት ስራ ሊያቆሙ መሆኑን የጋዜጣ አዙዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ መርካቶ፣ ሳሪስ፣ ቦሌና ካሳንቺስ የሚገኙ የጋዜጣ አዙዋሪዎች በርካታ አንባቢ የነበራቸው መጽሄቶችና ጋዜጦች ከገበያ በመውጣታቸው፣ ሌሎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች በማዞር ህይወታቸውን መምራት ስለማይችሉ የጋዜጣ ማዞር ስራቸውን አቁመው ሌላ ስራ ለመፈለግ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ በስርጭት ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው የነበሩት ፋክት፣ አዲስ ጉዳይና ሎሚን በመሸጥም ሆነ በማከራየት አብዛኛውን ገቢያቸውን ያገኙ እንደነበር የገለጹት የጋዜጣ አዙዋሪዎች አሁን ያሉትን ጋዜጦችና መጽሄቶች በህዝቡ ዘንድ እምብዛም ተነባቢ ባለመሆናቸው በዚህ ስራ ህይወታቸውን መምራት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ሚዲያዎቹን ከከሰሰ በኋላ ማተሚያ ቤቶች ቀሪዎቹን ጋዜጦችና መጽሄቶች አናትምም በማለታቸው በርካታ ሚዲያዎች ከገበያ መውጣታቸው ጋዜጣ አዙዋሪዎቹ ስራ እንዲያጡ ምክንያት መሆኑ ተገልጾአል፡፡

አዙዋሪዎቹ በእነዚህ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ከመወሰዱ በፊትም ቢሆን ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በመሆናችሁ የእነሱን አቋም የሚያንጸባርቁ ጋዜጣና መጽሄቶች ለህዝብ እንዲደርስ እያደረጋችሁ ነው፣ ከአጥፊ ኃይሎች ጋር እየተባበራችሁ ነው›› በሚል እርምጃ ይወሰድባቸው እንደነበርና አሁን በመጽሄትና ጋዜጦች ላይ የተወሰደው እርምጃ ሰርተው መኖር እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ የእነዚህ ሚዲያዎች በመዘጋታቸው የገቢ ምንጫቸውን ከማጣታቸው በተጨማሪም በሚዲያው ላይ የተወሰደው እርምጃ በእነሱም ላይ የማይወሰድበት ምክንያት እንደሌለ ባለፉት ጊዜያት የደረሰባቸው በደል ማሳያ መሆኑን በመግለጽ ስራውን ሊያቆሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ከወራት በፊት ገዥው ፓርቲ የሚቀጥለው ምርጫ ተከትሎ ሚዲያዎች ወደ ክፍለ ሀገር እንዳይደርሱ አከፋፋዮችንና አዙዋሪዎችን በማደራጀት ሚዲያዎችን ከስራ ለማስወጣት እንዳቀደ መገለጹ ይታወቃል፡፡