ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል

 

የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅትአንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩአለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራትበፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡
የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!
ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል
ዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎች
ነጻነትና ዳቦ – በናትናኤል ፈለቀ
ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል – በናትናኤል ፈለቀ
ስደትና ፍቅር – በሰለሞን አብርሃም(ከአውሮጳ)
ዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….? – በበፍቃዱ ሃይሉ
ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት? – በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤል
እኛና ሶማልያ – በናትናኤል ፈለቀ
ድምፃችን ይሰማ – በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤልና እና በፍቃዱ ሃይሉ
እንዴት እንደመጥ – በማህሌት ፋንታሁን
የመለስ ውርስ እና ራዕይ – በሶሊያና ሽመልስ
የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራ – በማህሌት ፋንታሁን
ትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ? -በበፍቃዱ ሃይሉ
ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ በዘላለም ክብረት
ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ
ከ21 አመት በኋላ ዴሞክራሲ ሲሰላ
ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መመሪያ በማክበር መሥራት ይቻላል?
አብዮት ወረት ነው
የእህአዴግ ‹‹ትርፍ›› እና ኪሳራ
የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች
ከእከሌን አሰሩት እስከ እከሌን አገዱት
ሰማኒያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
“ድር ቢያብር” ለአምባገነኖች ምናቸው ነው ?
ከሌሎች ብዙ ዝርዝሮች በጥቂቱ
“ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ ትግሬያዊ ማንነት የለም” – (በአብርሃ ደስታጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
“መንግስት የለም ወይ ?” የምንና ምን አይነት መንግስት(የመስፍን ነጋሽጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
የሁለተኛው ዘመቻ ዕቅድ ( ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
የ2ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
ዳዊት ሰለሞን ስለአዲሱ የጋዜጠኞች ፎረም ፕሬዚዳንት ፌስቡክ ላይ የፃፈው እና አጥናፍ ለበፍቄ ኢሜል የደረገለት ጽሑፍ
“ፍርሃታችንየት ያደርሰናል ?” በሚል በኤልያስ ገብሩ ተጽፎ በፍቄ ላፕቶፕ ውስጥ የተገኘ(ለዕንቁ መጽሄት ተዘጋጅቶ ያልታተመ ጽሑፍ)
የ3ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ( ዴሞክራሲን በተግባር እናውል የሰላማዊሰልፍ መብታቸን ይመለስ)
“ሰልፍና ሰይፍ ” በሚል በበፍቄ ተጽፎ ነገር ግን ያልታተመ ጽሁፍ ከላፕቶፑ
የ1ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ(draft ሕገ መንግሰቱ ይከበር)
የ4ኛው ዘመቻ ዕቅድ( ኑ ኢትዪጲያዊ ህልም አብረን እናልም)
ጋዜጠኛ አስማማው ለድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ያዘጋጀቸው ጥያቄዎችከኢሜሉ (ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት)
ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.org ላይ የታተሙጽሑፎች
በናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19 የተላከ 48,170.25(ብር) የዌስተርን ዩኒየን ኮፒ
“የተቃውሞሰልፉ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች” በሚል አዲስ ጉዳይ ላይ የታተመ ጽሁፍ (draft)
ማሒ ስለ ርዕዮት ዓለሙ እና ስለ አዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት ” በቀልድየጻፈችው ጽሑፍ፡፡
የዞን 9 ወደፊት ለመስራት የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክት ፕሮፓዛሎች ( ምርጫ2007 ሪፓርት የማድረግ ስራ፣ የኢትዮጲያ የነጻነት ኢንዴክስ ማዘጋጃት ስራ ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጲያ ላይ ለመስራት የታሰበ ዶክመንተሪእቅድ)
እና ሌሎችም ትርኪሚርኪዎች (ለምሳሌ የዳንኤል ብርሃነ ጽሑፍ፣ የናቲ የ10ኛክፍል ግጥም) Ewnetu Taye

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s