የሚስተር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉብኝትና አንድምታዉ

John Kerry official Secretary of State portrait.jpg

– አበባዉ መሐሪ– የመኢአድ ፐሬዚደንት

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሚስተር ጆን ኬሪ በቅርቡ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡ በዚህ ጉብኝታቸዉ ወቅትም በኢትዮጵያ እየደረሰ ባለዉ የሰባዊ መብት ጥሰት ላይ ብዙም ሳይሉና የተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን በሁኔታዉ ላይ ሳያነጋግሩ በመሔዳቸዉ ብዙዎችን ሳያሳዝን አልቀረም፡፡ በእርግጥ የእርሳቸዉ አመጣጥ በእርስ በእረስ ጦርነት በመታወክ ላይ ያለችዉን የደቡብ ሱዳን ችግር በመፍታት ላይ ያተኮረ ቢሆንም ቅሉ የኢትዮጵያዉያንን ችግርም ሳይቃጠል በቅጠል የሚል ምክር ለሁሉም ሊሰጡ በተገባም ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ የሚያመላክተን ምዕራባዉያን ብዙ ጊዜ የአገራቸዉን ጥቅም ሊነካ ለማይችል ችግር ብዙም ትኩረት የማይሰጡ መሆኑን ነዉ፡፡

እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የራሷ የሆነ ባህሏንና ቋንቋዋን አስከብራ በመኖሯ፣ እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የነጭ ሠራዊት በጦርነት በማሸነ÷ ¾}’d፣ ለአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ነጸብራቅ በመሆኗና፣ አሁንም የሰውን ልጅ እኩልነት እንጂ በዉጭ ሀይሎች የሚደረግን ጭቆናና ብዝበዛ ስለማትቀበል ምዕራባውያን መልካም ሲመኙላት ታይቶ አይታወቅም፡፡ በዚህ የተነሳም የውስጥም ሆነ የውጭ ባንዳ ቅጥረኞችን በመመልመል፣ የውስጥ ቅራኔን እየፈጠሩና በወኪሎታቸቸው በማስፋፋት ስለሚያስበጠብጧት ሰላም አጥታ ቆይታለች፡፡በዚህ የተነሳም ከልማት ይልቅ ለአገር መከላከሉ ቅድሚያ በመሰጠቷ ለኋላ ቀርነት ተጋላጭ አድረጓታል ።

ለዚህ መልካም ምሳሌ የሚሆነን በሁለቱም በኩል እፍኝ በማይሞሉ ፖለቲከኞች የተሳሳተ ውሳኔ የተነሳ እ.ኤ.አ በ1999 ዓ.ም የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከሰባ ሺህ የሚበልጡ ዜጎችን ሲበላ፣ ከሁለት መቶ ስድሣ ስምንት ሺህ በላይ ሰላማዊ ኗሪዎችን ሲያፈናቅልና በቢሊዮን የሚቆጠር ንብረትን ሲያወድም ምዕራባውያን በተገቢው ሰዓትና ወቅት በቂ የሆነ ‘‘የጦርነት አቁም!’’ ግፊት ሲያደርጉ አለመታያታቸዉ፣ ወይም ወደ ሰላም የሚያመራ የመፍትሔ ሀሳብ አለማመንጨታቸዉ፡፡ የብዙኃን መገናኛዎቻቸውም ቢሆን ጦርነቱ በከፋ ሁኔታ ይካሔድ በነበረበት ወቅት ለተፈጸመው የእንግሊዙ ልዑል(prince) ቻርልስ የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት የሰጡትን ያህል የዜና ሽፋን ለጦርነቱ ሊሰጡት አልፈለጉም ነበር፡፡ ይባስ ብለዉ ጦርነት በአፍሪካ እንደ ሕጻናት ጉንፋን የተለመደ ነዉ ብለዉ በመጻፍ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ አድርገዉታል፡፡

የኢትዮጵያው መለስ ዜናዊና የኤርትራው ኢሳይያስ አፈወርቂ ሥልጣን በጨበጡበት ወቅት በምዕራባዉያኑ ዘንድ የአዲሱ ትውልድ ወጣት መሪዎች የሚል የማሞካሻ ስያሜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ መሪዎች ሕዝባቸውን የቁም ስቃይ ሲያሳዩ፣ የነፃ ኘሬስ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን ሲያሳድዱ፣ ሲያፍኑና ሲያስሩ ምዕራባውያኑ ከይስሙላ ኘሮፓጋንዳና በአመታዊ ሪፖርቶቻቸው ላይ የሁኔታውን አስከፊነት ከመግለጥ በዘለለ በእነዚህ መሪዎች ላይ በቂ በሆነ ሁኔታ ‘‘የጭቆናህን አቁም’’ ግፊት ሲያደርጉ ወይም እርምጃ ሲወስዱ አልታዩም፡፡

በሁለቱ አገሮች ጋዜጠኞችና የተቀዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ላይ እስራቱና ግድያው በከፋ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር(Secretary of Defense) የነበሩት ሚስተር ዶናልድ ራምስፊልድ በአጥፍቶ መጥፋት (terrorism) ላይ የሚካሔደውን ጦርነት በምስራቅ አፍሪካ ለማጠናከር ኤርትራን በመጎብኘት ላይ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ በአሥመራ የአውሮኘላን ማረፊያ ይጠብቋቸው ከነበሩት ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጡ በነበረበት ወቅት፣ ከጥያቄዎቹ መካከል አንዱ ‘‘የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ወይም እንዳይገደሉ ለኤርትራ መንግሥት ምን ዓይነት መልዕክት ሊያስተላልፉ ይችላሉ?’’ የሚል ነበር፡፡ የእርሳቸው መልስ ግን፣ ‘‘ይህ የአገሪቱ መንግሥት የውስጥ ጉዳይ ነዉ’’ በሚል ደመደሙት፡፡ ይህ በግልጽ የሚያሳየን አንድ የሀገር መሪ የእነርሱን ፍላጎትና የሀገራቸውን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ እስከተገኘ ድረስ የሚመራውን ሕዝብ ቢጨቁን፣ ቢያፍንና ቢገድል ብዙም ደንታ አንደሌላቸው የሚያሳይ ነዉ፣ በተቃራኒው ደግሞ ለእነርሱ ያልተንበረከከ እና የእነርሱን ሀገር ጥቅም ለማስከበር ፈቃደኛ ያልሆነን የሀገር መሪ በጨቋኝነት፣ በዲሞክራሲ አፋኝነትና በጨፍጫፊነት ይፈርጁታል፡፡

ዲሞክራሲን በተመለከተ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ብዙም የጎላ ልዩነት እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ምዕራባውያን ኤርትራን ከብዙ ጉዳዮች ሲያገሉ የኢትዮጵያ መሪዎች የሰባዊ መብት ጥሰታቸዉን እንዲያቆሙ አንኳ በቂ ግፊት ሳያደርጉ ከእነረሱ ጎን መቆማቸዉም ለዚህ ዋና ምስክር ለመሆኑ በግልጽ የሚያሳየን ነዉ፡፡

ሌላኛው መሠሪ ዘዴያቸው ደግሞ፣ የአንድ ሀገር መሪ ሥልጣን ተረክቦ ሕዝቡን በሰላማዊ መንገድ ለማስተዳደር ሲሞክር ስልታዊ በሆነ መንገድ የተዛባ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ወይም የማህበራዊ ፖሊሲ እንዲያራምድ እየመከሩ ከሚመራው ሕዝብ ጋር በከፋ ቅራኔ ውስጥ እንዲገባ ከአደረጉት በኋላ በእነርሱ ጉያ ውስጥ እንዲሸጎጥ በማድረግ እነርሱ የፈለጉትን እንዲፈፅም ተጋላጭ ያደርጉታል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ የሚያሳየን፣ እነርሱ ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚመለከቱት ከራሳቸው የአጭርና የረዥም ጊዜ ስትራተጅካዊ ጥቅም ጋር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን የየራሳቸዉን የውስጥ ችግሮች በራሳችዉ ለመወጣት መጣር እንጂ ከምዕራብ አገራት ብቻ መፍትሄ መጠበቁ የሚያዋጣ መንገድ አለመሆኑን መረዳት አለባቸዉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ሕዝቡ ተሃድሶን በተጐናፀፈ አዲስ መልክ ዘረኝነትንና መለያየትን በመተው አንድነትና ስምምነት በመፍጠር በጋራ ለአገር ሊሠሩ በሚያስችላቸው ስልት ላይ መስማማትና የአፈፃፀም ግዴታ ውስጥ መግባት የግድ ይላቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለወደፊቱ ትውልድ ጥሩ አርአያነትን፣ የአመራር ብልህነትንና ለአገርና ለሕዝብ አሳቢነትን የሚያመላክት ስለሆነ በዚህ ላይ ሊበረታበት ይገባል እላለሁ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: