የኢተዮ ጅቡቲ ባቡር ሃዲድ መስመር 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ብረት ተዘረፈ ተባለ

August 3, 2014

የኢተዮ ጅቡቲ ባቡር ሃዲድ መስመር 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ብረት ተዘረፈ ተባለ
አዳማ ከተማ አካባቢ የሚገኘው የድሮው ሃዲድ እየተሸጠና እየተመዘበረ ነው ተባለ፡፡
በአዳማ የባቡር መስመሩ ሃላፊ የሆኑት አዲስ ዓለማየሁ ለሪፖርተር እንደተናገሩት በሞጆና በአዳማ መካከል ያለው የሃዲድ ብረት በግለሰቦች እየፈረሰና እየተሸጠ ነው፡፡ ኃላፊው አያይዘው እንደገለጹት በአዳማና በወለንጪቲ መካከል ያለውን መስመር ጨምሮ ሌቦች ብረቱን የሚሸጡት አዳማና ቆቃ አካባቢ ለተቋቋሙ የቻይና ድርጅቶች ነው፡፡
ሁለት ሚሊየን ብር ሚሆን የገንዘብ ተመንያላቸውየሃዲድ ብረቶች በፌደራል ፖሊስ ትብብር ከተለያዩ ቦታዎች ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡በፌደራል ፖሊስ ትብብር የተመሰኑ ግለሰቦች መያዛቸውንና ለህግ መቅረባቸውንም በመጠቆም፡፡
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር በ2010 ስራውን አቁሟል፡፡
ለባቡር መስመሩና ለሌሎች የድርጅቱ ንብረቶች የጥበቃ ኀይል ለመመመደብ በጀት እንደሌለ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡የተለያዩ ግለሰቦችም በመስመሩ ላይ ቤት እንደገነቡና አዳማ ከተማ አስተዳደር ቦታውን ለመውሰድ በመፈለጉ እሰጥ አገባ ውስጥ ነንጉዳዩንም ለተቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ይግባኝ አመልክተናል ብለዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s