ሰበር ዜና አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ August 5, 2014 የሆስፒታል ቀጠሮቸውን ያጠናቅቃሉ ! « በአቶ በረከት ጉዳይ ካድሬዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤትን ሲያምሱ ዋሉ »

August 5, 2014

ሳውዲ አረቢያ በህክምና ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስሞኦን ከህመማቸው አገግመው ሼክ አላሙዲን ወደ አዘጋጁላቸው ሚስጥራዊ ሆቴል ካቀኑ ወዲህ እኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስላሉበት የጤነነት ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻለም ከሁለት ቀን በፊት የሼክ አላሙዲን ወደ አመሪካ ማቅናት ተከትሎ የአቶ በረከት ስሞኦን የ ጤንነት ሁኔታ በመላካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ ። አቶ በረከት ስሞኦን እስካሁን ሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር በስልክም ሆነ በአካል እንዳለተጋናኙ የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች እኚህ የመንግስት ከፍተኛው ባለስልጣን ያረፉበት ሆቴል ምሲጥራዊነቱ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠበቀ መሆኑን ይናገራሉ።፡፤
የአቶ በረከት የጤንነት ሁኔታ በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ ከሆነ ወዲህ ጭቀት ውስጥ የገቡት ሼክ አልሙዲን የተለያዩ ሆቴሎችን እየቀያየሩ እኚህን የመንግስት ባለስልጣን ደብቀው ሲያስታምሙ እና አሰፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉላቸው መክረማቸውን ለማውቀ ተችሏል። አቶ በረከት ከሆስፒታል ከወጡ ወዲህ የተለያዩ ሆቴሎች እንዳረፉ የሚገልጹ መረጃዎች ሼኩ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው በፊት በግል ከተከራዩላቸው ምርጥ ሆቴሎች ምናልባተም የመጨረሻ የአቶ በረከት ሚስጥራዊ ማገገሚያ ይሆናል ተብሎ ከሚነገርለት ሆቴል ነገ ወደ «ቡግሻን» hospital በማቅናት የመጭረሻ የህክምና ቀጠሮአቸውን ካጠናቀቁ በሃላ በአጭር ቀን ውስጥ፡ ወደ ሃገር ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘ ዜና በህክምና ላይ የምትገኘው የ6 አመቷ የአቶ በረከት ልጅ ህጻን ህሊና በረከት በመልካም ጤነት ላይ መሆኗን የኢትዮጵያ ሃገሬ የሆስፒታል ምንጮች አረጋግጠዋል ።
ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የአቶ በረከትን ገበና አጋለጣችሁ በሚል ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ዛሬ የመጡ ኢትዮጵያውያን ሲያዋኩብ መዋላቸው በጅዳ እና አካባቢው ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ማስነሳቱ ን ለማረጋገጥ ተችሎል ። ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የተለያዩ ጉዳዮቹን ለማስፈፀም በጠራራ ጸሃይ ሲነፍሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ዜጋ አዝነው በአግባቡ ከማስተናገድ ይልቅ አቶ በረከት መታመማቸውን መረጃ ያወጣችሁት እናንተ ናችሁ የተቃዋሚ ወሬ አቀባዩች እናተን ሰብስቦ ማቃጠል ነበር በሚል ዛቻ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል የድርጀት አባል በማይጠበቅ ቃላት በኢ.ህ.ዴ.ን ካድሬዎች እና የህወሃት ካድሬዎች ሲዋከቡ መዋላቸውን በደሉ የተፈፀመባቸው ወገኖች ገልፀውልናል። በተለይ እራሳቸውን ብቸኛ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ፈላጭ ቆራጭ አድርገው ያስቀመጡት የህወሃት የቀድሞ ታጋይ አቶ ገሬ እና መዝገብ ቤት ሃላፊ የሆነው የትግራይ ተወላጁ የቀድሞው የህወሃት ታጋይ የአሁኑ የአማራ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ሽፋ ባለጉዳዮችን ሲያንገራግሩ ከነብሩ መሃከል ግንባር ቀደም እንደነበሩ ታውቋል። የጅዳ ቆንስል ሃላፊ የነበሩትን ቆንስል ዘነበን በተጽዕኖ ያስነሱት እንዚህ የጅዳ ኢህአዴግ ካድሬዎች የጅዳን ቆንስላ ጽ/ቤት በመቆጣጠር ዲፕሎማቶችን በመናቅ እንዳሻቸውለማዘዝ ከመቃጣታቸውም በላይ ለጉዳይ የመጣውን ኢትዮጵያዊ በማጉላላት እና ፓስፖርት እስከ መንጠቅ የደረሱ ወንጀለኞች መሆናቸው በአብዛኛው የጅዳ ማህበረሰብ ዘንድ ይነገራል። ከዚህ መሰሪ ተግባራቸው ያልታቀቡት እንዚህ ግለሰቦች የአቶ በረከትን ለህክምና መምጣትን መረጃ አወጣችሁ የሚሏቸውን ወገኖች ወደ ቆንስላው ግቢ ሲገቡ በመተናኮል ሁከት ቀሰቀሱ ብለው ለማሳሰር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከጽ/ቤት የወጡ መረጃዎቻችን ጠቁመዋል።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s