አሸባሪው የወያኔ መንግስት በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ ክስ መመስረ

 

በአንዳንድ የሕትመት ውጤቶች ላይ የወንጀል ክስ ተመሰረተ፡- ፍትህ ሚኒስቴር

የአሸባሪነት ታፔላ ለጥፎ ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን አሳዶ በማሰርና በማሰቃየት ነፃ ሚዲያን ከአገሪትዋ ለማጥፋት እየሰራ ያለው የወያኔ መንግስት በእኩይ ተግባሩ በመቀጠል በትናንትናው ለት በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ ወንጀል ክስ መመስረተ።
ለዚህም የሰጠው ምክንያት በህገ፡መንግስቱ የተደነገጉ ገደቦችን በመጣስ፤ ስራዬ ብለው ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመጽና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፤ አክራሪነትን እና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እና የሚያበረታቱ አሉ፡፡

ከዚህም ባለፈ በህዝቡ መካከል የዘር እና የሃይማኖት ጥላቻን የሚቀሰቅሱ፣ የህዝብ መሪዎችን እና ተቋማትን መልካም ስምና ዝና በሃሰት የሚያጠፉ የሚወነጅሉ አንዳንድ ህትመቶች መኖራቸው ይታወቃል ብሏል። አንዳንድ የሕትመት ውጤቶች ግን ማሻሻያዎችን ከማድረግ ይልቅ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድና ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የወንጀል ተግባሮቻቸውን ቀጥለዋል፡፡ክስ የማቅረቡ ሂደትም በተደጋጋሚ ሕጉን በማን አለብኝነት በጣሱ እና በሚጥሱ አሳታሚዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ላይ እንደሚቀጥል የፍትህ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሳታማሀኝ ብላኝ አለ ያገሬ ሰው እስኪ አሁን ማነው ከፋፋይ ማነው ዘረኛ ማነው ህዝብን በሀይማኖትና በብሄር በመለየት ለስልጣን ማቆያ  ይሆነው ዘንድ ሲያበጣብጥ የኖረው  እራሱ ያረቀቀውን ህገ፡መንግስቱን በመጣስ ሲገድል ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሲያስር ለ፪፫ ዓመታት ተሸክመነዋል ። ግፈኝነቱነ የቀጠለበት የወያኔው መንግስት የግሉ ፕሬስ የሆኑትን  ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ መጽሔቶች እንዲሁም አፍሮ ታይምስ በተባለው ጋዜጣ ላይ በዓቃቤ ህግ የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

source freedom4ethiopian

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s