በኦህዴድ ውስጥ የሚታየው ትርምስ ቀጥሏል

 

አብዛኛው የኦህዴድ አባላት በድርጅታቸው ብቃት እና በድርጅታቸው ህዝባዊ ተቀባይነት ላይ ያላቸው አመኔታ እጅግ የወረደ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው አብዛኛው የኦህዴድ ካድሬዎች ድርጅታቸው ብቃት የሌለውና በህዝቡ ዘንድ የተጠላ ነው ብለው ያምናሉ።

ካድሬዎቹ ህዝቡን ከድርጅቱ ጎን ለማሰለፍ እየከበዳቸው በመምጣቱ ብዙዎች ስራቸውንና ሃላፊነታቸውን እየለቀቁ ያለስራ መቀመጥን እስከመምረጥ ደርሰዋል። ድርጅቱ ስብሰባ ሲጠራ አብዛኛው ህዝብ ለመገኘት ፈቃደኛ ስለማይሆን፣ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኞችን እያስገደዱ ለስብሰባ እንዲወጡ እስከማስደረስ ደርሰዋል።
በቅርቡ የተከበረውን የሴቶች ሊግ በአል ለማዘጋጀት በታቀደበት ቀን በበአሉ ላይ የሚገኝ ሰው በመጥፋቱ፣ የበአሉ ማክበሪያ ቀን እንዲራዘም ከተደረገ በሁዋላ በሳምንቱ ካድሬዎች የመንግስት ሰራተኛ ሴቶችን አስገድደው እንዲያስወጡ ለመውጣት ፈቃደኛ ባልሆኑ ሴቶች ላይ ምዝገባ ተካሂዶ እንዲቀጡ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ከተሰጠ በሁዋላ፣ የተወሰኑ ሴቶች ተገኝተው በአዳማ በአሉን አክብረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዳማ ከተማ የደህንነት ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዋነውና ምክትሉ ከድርጅቱ አመራሮች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከስራቸው ተባረዋል።

ዋናው የደህንነት ሹም የነበሩት አቶ አብዶ ቀደም ብለው የተባረሩ ሲሆን፣ ሰሞኑን ደግሞ ምክትላቸው አቶ ጌታቸው ኦሊ እንዲባረሩ ተደርጓል። አቶ ጌታቸው ለግምግማ በተጠሩበት ወቅት የበላይ አለቆቻቸውን ሁላችሁም ሌቦች ሆናችሁ እኛን ልትገመግሙ አትችሉም ብለው መናገራቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

በአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ሲወሰድ ለነበረው እርምጃ ሁለቱ ባለስልጣናት ዋና ተጠያቂዎች መሆናቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። ሁለቱም ባለስልጣናት ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በተፈጠረ የጥቅም ግጭት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: