ተከብሮ ያላስከበረ፣ ሰርቶ ያላሰራ ‘ሕገ-መንግስት’

imgres    

ሕዝባዊ መንግስት ማለት ሕዝቡ በቀጥታ የራሱ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት ማለታችን ነው:: ህዝቡ መሪዎቹን በነጻ የመምረጥ እና የማዉረድ መብቱ የተረጋገጠበት ማለት ነው:: ሕዝባዊ መንግስት ስንል የመግስት ስልጣን መነሻ እና መድረሻው ህዝቡ ነው ማለታችን ነው::
ህገ መንግስት ደግሞ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ‘ህገ መንግስት’ እንደሚለው ከሆነ ‘ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገ መንግስቱ የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም።’ በኢትዮጵያ በሃገራችን ወያኔ አለኝ የሚለው ‘ህገ መንግስት’ምንም ኢትዮጵያዊነት የማይታይበት ጭንቅላቱ ከካናዳ፤ እግሩ ከሕንድ፤ እጁ ከአውሮፓ፤ ልቡ ከጫካ የተገጣጠመ ጽሑፍ ሰላማዊውን ህዝብ ያስፈራራል፤ ያሸብራል!
”ይህ ህገ-መንግስቱን የመናድ ተግባር ነው!!!” የሚለው ሃረግ ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል፥ የህዝቤን እንግልት ለአለም አሳውቃለሁ ላለ ለእውነት የሚሰራና የሚያገለግል ሃገር ወዳድ ዜጎችን ከጥፋተኝነት ለመፈረጅ ብሎም ለመክሰስ ወደ እስር ቤትም ለመወርወር የሚጠቀሙበት አረፍተ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ”ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው?” በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡ በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተው ‘ህገ መንግስት’ እጅግ በጣም ብዙ ንጹሃን ዜጎችን የማሰቃያ መሳርያ ሆኗል፡፡
እየተንገዳገደና ተደግፎ ያለው ‘ህገ መንግስት’ ከአረቃቀቁና ከአፀዳደቁ ጀምሮ ያልተስተካከሉ ድንጋጌዎች የመኖራቸውን ያህል ‘ፀድቆ’ም በተግባር ላይ የሚገኘው ‘ህገ መንግስት’ ዋጋ እንዳይኖረው፥ በግልጽ የተጻፉትን/የሰፈሩትን እንኳን በአግባቡ እንዳይተረጎም እያደረገ ያለው እራሱ የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር እንዲሁም የአሰራር ብልሹነት መሆኑን አለፍ አለፍ እያልን በአጭሩ ለማየት እንሞክር፥
1ኛ.  ”የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የጎሳዎች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡” ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 87/1 ተደንግጎ ይታያል፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የሠራዊቱ አባል እና አዛዦች የአንድ ጎሳ ስብስብ ናቸው፡፡
2ኛ.  ”የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ሆነ አካል ተፅዕኖ ነጻ በመሆን በሙሉ ነፃነት ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡” በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 79 እና በተከታዮቹ ንዑስ አንቀፅ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የመንግስት አስፈፃሚ አካል ከሆነው ነው ሹመታቸውን የሚያገኙት፡፡ በመሆኑም ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግኝኙነት ያላቸው የፍርድ ውሳኔዎች ምን ያኽሉ በህግ እና በህሊና ላይ የተመሠረቱ እንደሆኑ መገመት አያስቸግርም፡፡ በተለይ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የፍርድ ሂደታቸው ምን ይመስል ነበር? እነዚህን እና መሰል ዳኝነቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በህገመንግስቱ የሰፈረው የነጻ ዳኝነት አካል ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
3ኛ.  ”በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከሰዎች ወይም ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡” በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ነፃ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን እያየን እየታዘብንም ነው፡፡
4ኛ.  ”ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡” የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሃሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ነፃ ሃሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ? ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣ በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡ መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ብሎም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
5ኛ.  ”መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም” የሚለው በሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ገዢው መንግስት በሃይማኖት ላይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እየፈፀመ ይገኛል፤
6ኛ.  ”የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፡” የሚለው በሕገ መንግስት አንቀጽ 12 ንዕሱ አንቀፅ 1 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ ነገር ግን ከታችኛው የስልጣን እርከን ከሆነው ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይኛው የመንግስት ባለስልጣናት የሚከናወኑ የመንግስት የአሰራሮች ግልፅነት ፍጹም ጠባብ ነው፡፡
7ኛ.  ”ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው፡፡” ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 14 ላይ ተፅፎ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የሰው ደህንነትን ለመጠበቅ የተቋቋመው የደህንነት መስሪያ ቤት በተቃራኒው በየደኑና በየጫካው የስንቱን ሰው ህይወት እንዳጠፋና የአካል ጉዳት እንዳደረስ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ ”ሰው ሰብኣዊ” ሆኖ ከተፈጠረ በኋላ ማንነቱን/ሰብዓዊነቱን የሚያጣውም የሚያሳጣውም መንግስትና ፓርቲ ነው ማለት ነው!?
8ኛ.  ”ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት፣ ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡” የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 18 ላይ ይገኛል፤ ይህ የህገመንግስት ድንጋጌ መሸራረፍ ሳይሆን መገርሰስ የሚጀምረው በህገመንግስቱ በተቋቋመው በህግ አስፈጻሚው አካል ነው፡፡
9ኛ.  ”ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ ሠላማዊ ሠልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡” ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 30/1 ላይ ይገኛል፡፡ በመንግስት እየታየ ያለው የአስተዳደር ብልሹነት ለማመልከት እና ምላሽ ለማገኘት የተጠሩ የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች እና ስብሰባዎች በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ ተከልክሏአል፡፡
10ኛ.  ”በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡” የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስት በፍጹም ያደላ ነው፡፡ ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ብሎ ማለት ትልቅ ስህተት ነው፡፡
11ኛ.  ለዚህም ነው ”ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገመንግስቱ የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡” የሚለውን አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 የገዥው መንግስት ደራሽ ዉሃ ጠራርጎ ወስዶታል የምንለው::

ለዚህ ገጽ እንዲመች ተደርጎ እና ከ http://www.goolgule.com/a-constitution-of-no-good/ ላይ ተቀንጭቦ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: