ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ)

FREEDOM 4 ALL ETHIOPIANS

August 7, 2014
ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ)

ትላንት በአዲሳባ የሚገኙ ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ሂሳብ እያንከበከቡ በመሸከም መንግስት በፈጠረላቸው አስፋልታዊ ጎርፍ ላይ ሲያሻግሩ ዋሉ። ወጣቶቹ፤ ”መንግስታችን አስፋልት እንጂ የውሃ መተላለፊያ ያልሠራው አቅቶት ሳይሆን ለእኛ አስቦ በመሆኑ ምን ያህል ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ሲሉ ለመንግስታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

”መንግስት ለቀጣይ ክረምቶችም የውሃ ፍሳሻቸው ያልተዘጉ መንገዶችን ቱቧቸውን በመዝጋት የእኛን እንጀራ እንደሚከፍትልን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉም በስራ ፈጠራው ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ገልጸውልናል።

የአዲሳባ አስተዳደር በበኩሉ፤ ዛሬ በአስፋልት ላይ የታየውን ጎርፍ በአምስት አመቱ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በየቤቱ ለማስገባት እንደሚጥር ይሄም በርካታ ዜጎችን ለስራ ፈጠራ እንደሚያነሳሳ ገልጿል።

እያልን እየቀለድን የትላንትናውን የአዲሳባ ቦሌ መንገድ ውሎ የምታስቃኝ ቪዲዮ እንካችሁ በታደሰ አለሙ አራዳ ሙዚቃ ታጅባለች።

posted by Daniel tesfaye

View original post

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s