ከ328 ሺህ ብር በላይ አጭበርብረዋል የተባሉ የቴሌኮም ሠራተኞች ተከሰሱ

በአሸናፊ ደምሴbirr4123111

በኢትዮ-ቴሌኮም አዲስ አበባ ቅርንጫፍና በደቡብ አዲስ አበባ የሃና ማርያም ቅርንጫፍ ሠራተኞች የነበሩ ሁለት ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ አስር የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች የፌዴራሉ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ የደንበኞችን የሞባይል ሲም ካርድ ኮዶች በመስበር ከተለያዩ ባንኮች በሀዋላ የተላከን ከ328 ሺህ ብር በላይ በተጭበረበረ መንገድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ሲል ክስ መስርቶባቸዋል። ትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ክሳቸው በተነበበላቸው 10 ተከሳሾች መካከል አራቱ ብቻ በችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ ቀሪ ስድስቱ በመጥሪያ እንዲቀርቡ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቶባቸዋል።

ክሱ በችሎት ሲቀርብ የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክሱን ያተተው፤ ተከሳሾቹ እርስ በእርሳቸው የጥቅም ተጋሪ በመሆንና የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው። ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ፤ 1ኛ ተከሳሽ አማኑኤል አለሙና 2ኛ ተከሳሽ ዮናስ ኃይሉ በቴሌኮም ካርድ ሽያጭ መደብ ውስጥ በማገልገል ላይ ሳሉ ከሶስተኛ እስከ አስረኛ ከሚደርሱት ግብረአበሮቻቸው ጋር በመመሳጠር ከተቋሙ የሲም ካርድ ግዢን ከሚፈፅሙ ደንበኞችን “የፒን” እና “የፒዩኬ” ኮዶችን በምስጢር በመስበር በሃዋላ የሚላክላቸውን ገንዘብ ጠልፈው መልእክቱን ካደመጡ በኋላ የደንበኞቹ ግንኙነት እንዲቋረጥ በማድረግ፤ የተሳሳተ መታወቂያ በመጠቀም ከ328ሺ ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው በማዋል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ይላል።

የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በአስር ግለሰቦች ላይ ክሱን ቢመሰርትም ሁለቱን የቴሌኮም ባልደረቦች ጨምሮ ሌሎች ስድስት ተከሳሾች በችሎቱ ያልቀረቡ ሲሆን፤ በችሎት ተገኝተው ክሳቸውን ያደመጡት 3ኛ፣ 4ኛ፣ 7ኛ እና 10ኛ ተከሳሾችም ለፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ ከ10 ዓመት በላይ በሆነ እስር የሚያስቀጣቸው በመሆኑ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎትም የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ያልተያዙት ተከሳሾችም እንዲቀርቡ በማዘዝ ለነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

One thought on “

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: