የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብራዚል ገባ

ኢ.ኤም.ኤፍ) ለሚቀጥለው 2015 ዓ.ም፣ በሞሮኮ ለሚደረገው የአፍሪቃ ዋንጫ ዝግጅት እና ልምምዱ ካሁኑ ተጀምሯል። ኢትዮጵያ ማጣሪያ የምታደርግበት ቡድን ውስጥ ማላዊ፣ ማሊ እና አልጄርያ ይገኙበታል። ከነዚህ የአፍሪቃ አገሮች ውስጥ ደግሞ በተለይ አልጄርያ ባለፈው የአለም ዋንጫ ከፍተኛ ከሌሎች የአፍሪቃ አገሮች በተሻለ መልኩ ውጤት ማስመዝገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያም ቡድን በዚህ ምድብ ውስጥ የመጀመሪያውን ጨዋታ የሚያደርገው ከዚሁ ከአልጄርያ ቡድን ጋር ነው። እናም የኢትዮጵያ ቡድን ራሱን ለማዘጋጀት እና ከሶስት የተለያዩ የብራዚል ቡድኖች ጋር 5 የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ነው ወደ ብራዚል ያቀናው።

Ethiopian team in brazil

በዚህ የሁለት ሳምንታት ቆይታ ወቅት ከ AC Anapolina Club Do Remo፣ Brasiliense እና በመጨረሻም ከ Itubiara ይጫወታል። አዲሱ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ እና ረዳታቸው ዳን ኤል ጸሃይ፣ የቡድኑ ሃኪም ዶ/ር ተረፈ ጣፋ እና በሃይሉ አበራ ብራዚል ገብተዋል።

ከተጨዋቾቹም መካከል አሁን ብራዚል የገቡት፤ በረኞቹ ጀማል ጣሰው እና ሲሳይ ባንጫ ሲሆኑ ሌሎቹም ተጫዋቾቾች፤ ኤፍሬም አሻሞ፣ መሱድ መሃመድ፣ ሽመልስ ተገኝ፣ አንዳርጋቸው የላቀ፣ ጾክ ጄምስ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ብርሃኑ ቦጋለ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ አክሊሉ አያናው እና ዳዋ ሆጤሳ አሁን ብራዚል ይገኛሉ።

ዛሬ ከአዲስ አበባ ተነስተው ብራዚል የሚገቡት ደግሞ ምንያህል ተሾመ፣ አስራት መገርሳ፣ ሳላዲን በርጌቾ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ፍቅሩ ተፈራ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ ፍጹም ገብረማርያም፣ በሃይሉ አሰፋ፣ አዳነ ግርማ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ፋሲል ተካልኝ እና ሌላኛው ረዳት አሰልጣኝ ኃይለስላሴ ጊዮርጊስ ከተጫዋቾቾቹ ጋር ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ይነሳሉ።

ኢ.ኤም.ኤፍ. በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ቡድን መልካም ምኞት በማስተላለፍ ዜናውን እዚህ ላይ ያበቃል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: