አቶ በረከት ስሞዖን ከወር በኃላ ለምርመራ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደሚመለሱ ተገለፀ !

August 12, 2014

የልብ ህክምናቸውን ጨርሰው ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት አቶ በረከት ስሞዖን የጤንነታቸው ሁኔታ ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ላይ መሆኑን የሚያመለክቱት በሳውዲ አረቢያ «የቡግሻን» ሆስፒታል ምንጮች ባለስልጣኑ በአፋጣኝ ህክምና ተደርጎላቸው ባይሆን ኖሮ በሽታው ሙሉ ለሙሉ ሽባ « ፓራላይዘድ » ሊያደርጋቸው ይችል እንደ ነበር ይገልጻሉ። ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ የሚገኝ በተለምዶ «ቡግሻን ተብሎ የሚጠራ ሪፈራል hospital » ውስጥ የኚህን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የልብ ችግር ለመፍታት ከ 6 ሰዓታት በላይ ህክምና መውሰዱን የሚናገሩ የሆስፒታሉ ምንጮች የልብ ቦንቦውን የምሳፋት ስራ የተሳካ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ቢሆንም አቶ በረከት የጤንነት ሁኔታቸው በማህበራዊ ገጾች መነጋገሪያ መሆኑ ተከትሎ በውስጣቸው የፈጠረው ጭንቀት ከህክምናው በኃላ የልብ ምታቸው ለውጥ ባለማሳየቱ በህክምና ባለሙያዎቹ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር አክለው ገልጸዋል ። በልብ ዙሪያ የሚከሰቱ ችግሮች ዋስትና እንደሌላቸው የሚናገሩ አንዳንድ የሙያው ጠበብቶች የልብ ቦንቦ ቸገር አብዛኛውን ግዜ የሚከስተው ከውፍረት እና ከደም መርጋታ ጋር ተያይዞ መሆኑን በመጥቀስ በሽታው « በግራ በኩል የሚገኘውን የሰውነት ክፍል ባልታሰበ ግዜ ሙሉ ለሙሉ ሽባ « ፓራላይዝድ በማድረግ እስከሞት ሊያደርስ የሚቸል አደገኛ በሽታ መሆኑን በመጥቀስ ።
በተመሳሳይ መልኩ የኚህን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የጤንነት ሁኔታ በቀጣይነት ለማረጋገጥ፡በየወሩ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባቸው ይናገራሉ ። ሰሞኑንን ባህርዳር የብሄር አማራ ዴሞክራሲ ንቅናቄ « በ.አ.ዴ.ን » ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሊትዮጵያ ህዝብ በመንግስት መገኛኛ ብዙሃን የታዩት አቶ በረከት የፊታቸው ገጽታ መልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ቢገልጽም በአጋጣሚ ህይወታቸውን ሊያሳጣቸው ከሚችለው የልብ በሽታ እራሳቸውን ለመታደግ የጤና ምርመራ «ቼክ አፕ» ለማድረግ ከወር በሃላ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደሚመለሱ ለማወቅ ተችሎል። የአቶ በርከት ስሞዖን ቀጣዩ የሳውዲ አረቢያ የጤና ምርመራ ጉዛ ጅዳን አልፎ ሪያድ ሊዘልቅ እንደሚቸል የሚገልጹ ውስጥ አውቂ ምንጮች እኚህን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ሼክ አላሙዲን በሳውዲ መንግስት በኩል በፕሮትኮል ለማስገባት እቅድ እንዳላቸው አክለው ተናግረዋል። በሼኽ አላሙዲን የግል አይሮፕላን በድብቅ ሳውዲ አረቢያ ገብተው ህክምናቸውን ሲከታተሉ ለቆዩት አቶ በረከት ስሞዖን እስካሁን 60 ሺሕ የሳውዲ ሪያል « መውጣቱን እና ጠቅላላ የህክምን ወጪውም በሼኩ ሙሉ ለሙሉ መሸፈኑን ለማረጋገጥ ተችሎል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s