አቶ ሙሼ ሰሙ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ለአለፉት 15 ዓመታት በዋና ጸሃፊነት፣ በህዝብ ግንኙነትና በፕሬዚዳትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ፤ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ ው አገለሉ፡፡

“ራሴን ከፖለቲካ ያገለልኩት ፋታ በመውሰድ ቆም ብዬ ስለትግሉ ሂደትና ወደፊት ማድረግ ስላለብኝ ነገር ማሰብ ስለምፈልግ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ እንደማንኛውም ሰው ስለቤተሰቤ፣ ስለትምህርቴ፣ ስለህይወቴ ማሰብ ያስፈልገኛል” ብለዋል፡፡
በቀጣይ በትርፍ ጊዜያቸው የኢዴፓን አላማና አቋም ለማጠናከር እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ ሙሼ፤ አሁን ያሉት አመራሮች የፓርቲውን የፖለቲካ ስራ በአግባቡ እንደሚወጡ፣ ትግሉንም እንደሚቀጥሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
“እንደ ፓርቲ አባልነት ሃላፊነት ወስጄ ባይሆንም በፍላጎት በፖለቲካ ውስጥ የራሴን ሚና እጫወታለሁ” ያሉት አቶ ሙሼ፤ “የፖለቲካ ትግሌም ሆነ ድጋፌ ከሌላ ፓርቲ ጋር ሣይሆን ከኢዴፓ ጋር የተሳሰረ ይሆናል” ብለዋል፡፡
ኢዴፓን ለ5 ዓመት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ሙሼ፤ ባለፈው ዓመት ከሃላፊነት የለቀቁ ሲሆን በፓርቲው ውስጥ እስከ ዛሬ የቆዩት ፓርቲው ጊዜና ትንፋሽ ሳያገኝ መልቀቅ ባለመፈለጋቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s