የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና ሌሎች ታሳሪዎች ችሎት በሲ.ኤም.ሲ ዲቦራ ት/ቤት እስከ ረፋድ ድረስ ተካሄደ!


የኮሚቴዎቹ ችሎት ዛሬ እስከ ረፋድ ቀጥሎ ዋለ!
3 የመከላከያ መስክሮች ምስክርነታቸውን አሰምተዋል!
‪#‎ድምፃችን‬ ይሰማ —- ማክሰኞ ነሃሴ 13/2006
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና ሌሎች ታሳሪዎች ችሎት በሲ.ኤም.ሲ ዲቦራ ት/ቤት እስከ ረፋድ ድረስ ተካሄደ! በዛሬው ችሎት እንደለተለመደው የተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮች የተደመጡ ሲሆን በችሎቱ የተገኙት ሶስት ምስክሮችም በተመሳሳይ ጭብጥ ላይ ምስክርነት አሰምተዋል፡፡ ምስክሮቹ ናዲያ አብደላ፣ ሙሂዲን ጀማልና አክሊሉ ሲሆኑ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላቱ በአወሊያ መድረኮች ምን ምን መልእክቶችን ሲያስተላልፉ እንደነበር በሚያስረዳው ጭብጥ 4 ላይ ዝርዝር ምስክርነታቸውን አሰምተዋል፡፡

የመከላከያ ምስክሮቹ በአወሊያ ሳምንታዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ፕሮግራሞች ላይ መገኘታቸውን ገልጸው ተመራጭ የኮሚቴ አባላቱ በተለያዩ ጊዜያት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸውን ውይይቶች ለህዝቡ በምን መልኩ ሪፖርት ያደርጉ እንደነበር ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ በዋነኝነትም መንግስት ‹‹ኮሚቴዎቹ ኹከት ቀስቃሽና ‹ኢስላማዊ መንግስት እንመሰርታለን፤ ‹ጂሃድ እናውጃለን› ብለው ንግግር አድርገውባቸዋል›› ባላቸው ጥር 11፣ ጥር 18፣ የካቲት 30 እንዲሁም የመጋቢት አጋማሽ ቀናት ላይ ኮሚቴዎቹ መንግስት ከሚለው ፈጽሞ የራቁ ሰላማዊ ንግግሮችን ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ በመድረኩም ከመንግስት ጋር እየተደረገ ያለው ውይይት ተስፋ ሰጪና መሆኑን እና ለሙስሊሙ ጥያቄ መንግስት ተገቢውን አዎንታዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ተስፋ እንዳላቸው ደጋግመው ይናገሩ እንደነበር ያስረዱት ምስክሮቹ በአወሊያ መድረክ ላይ ላይ ይደረጉ የነበሩት ንግግሮችና ዳእዋዎች መቻቻል፣ ሰላምና ፍትህ ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ አስገንዝበዋል፡፡

በዛሬው ችሎት የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኃላፊ በእነ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ እየወሰዱት ስላለው ህገ ወጥ እርምጃ ራሳቸው በአካል መጥተው በደብዳቤ ምላሽ እንዲሰጡ በታዘዘው መሰረት ከብዙ ቀናት እምቢታ በኋላ በዛሬው እለት መጥተው በደብዳቤ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሐሙስ ነሃሴ 15 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ችሎቱ ከተፈጸመ በኋላ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር ውጪ የችሎቱ ታዳሚዎችም ሆነ ታሳሪዎች ከችሎት አዳራሽ ሳይወጡ በፊት በካቴና እንዲታሰሩ መደረጉ በቦታው የነበሩትን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት አሳዝኗል፡፡

ችሎቱ በነገው እለት በተመሳሳይ ቦታ ከጠዋቱ ጀምሮ ቀጥሎ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s