ኢህአዴግ አክራሪነትን ለመዋጋት አዲስ ስታራቴጂ መንደፉን አስታወቀ

 

ኢሳት ዜና :-በእስልምና በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች እየታየ ያለው የአክራሪነት አደጋ ለስርዓቱ ፈተኝ ሆኗል በሚል አላማ የተሰናዳው አዲስ ስትራቴጂ በአማራ፣ በኦሮምያና በደቡብ ክልሎች ከመጪው አመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።
በሰነዱ ዙሪያ ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን እና ለአክራሪነት ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የአንዳንድ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የተለያዩ መስሪያ ቤት አመራሮች ውይይት አድርገውበታል።
ውይይቱን የተካፈሉት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት የላኩት የሰነድና ድምጽ ማስረጃ እንደሚያሳየው ገዢው ፓርቲ አክራሪዎች ናቸው ባላቸው ሃይሎች ፈተናዎች ተደቅነውበታል።
በውይይቱ ላይ እስካሁን መንግስት አክራሪ ባላቸው ሙስሊሞች ላይ የተወሰዱት እርምጃዎች ተነስተው የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሼህ መሃመድ ሃሰን በተገኙበት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የደቡብ ወሎ አስተዳዳርና ጸጥታ ዘርፍ ም/ል ሃላፊ በውይይቱ ላይ ” ትናንት ያገኘናቸውን መስኪዶች ዛሬ እያጣናቸው ነው፣ በአክረሪው ተይዘው የነበሩትን መስጊዶች ብንወስዳቸውም ተመልሰው ወደ አክራሪዎቹ እየሄዱ ነው።” ነው ብለዋል። ም/ል ሃላፊው አክለውም የሃይማኖት አባቶችን ብቃት ለማሳደግ የፖለቲካ አመራሩ እገዛ ማድረግ እንዲሁም በመጪው ምርጫ ድርጅቱ ችግር ውስጥ እንዳንገባ ከአሁኑ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል።
ሌላ አመራር ደግሞ ” በ2005 በተደረገው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ የመንግስት ሰራተኛው በምክር ቤት እንዲደራጅ ቢደረግም ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ አይደለም ካሉ በሁዋላ፣ የእስልምና ምክር ቤቱን በተዘረጋለት መዋቅር መሰረት በበቂ ሁኔታ እየሰራ ባለመሆኑ መንግስት ሊያጠናክረው እንደሚገባ” ተናግረዋል።
በስብሰባዎቹ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች የክልሉ አስተዳዳርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ ፣ የርእሰ መስተዳድሩ የከተሞች የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ፣ የአድማ ብተናና ጸረ-ሽብር ግብረ ሃይል ዋና የስራ ሂደት መሪ ረዳት ኪሚሽነር ደስዮ ደጀን በተጋገዝ መልስ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ ስላለው አክራሪነት በኢህአዴግ አመራር ውስጥ ከፍተኛ ብዥታ እንዳለ ገልጸው፣ የዘመቻ ስራ ካልተሰራ በስተቀር በሚጪው ምርጫ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ኪሚሽነሩ አክለውም በመጪው ምርጫ ህዝቡ ድንጋይ መወርወሩን ትቶ በዝምታ ሊያልፈው እንደሚችልና ይህም ቢሆን ለስርዓቱ ትልቅ አደጋና ውድቀትን ያመጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል የመድረኩ መሪ በበኩላቸው መጅሊሱንና መስጊዶችን ብንቆጣጠራቸውም አክራሪዎችን ህዝቡን በማህበራት ገብተው ይዘውታል ካሉ በሁዋላ ትግሉ ለመጅሊስ ብቻ መተው እንደሌለበትና መንግስት በቀበሌ፣ በአንድ ለአምስት አደረጃጃትና በተለያዩ የተዋረድ ስራዎች ገብቶ ስራ ለመስራት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ውይይቱ ከ3 ሰአት በላይ የፈጀ በመሆኑ፣ በውይይቱ ላይ የተነሱትን ሃሳቦች እንዳስፈላጊነቱ ለወደፊቱ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።
መንግስት በ2005 የተደረገው የእስልምና ምክር ቤት ምርጫ ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ መከናወኑን እንዲሁም በሃይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል።

posted by Aseged Tamene

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: