መንጌ በራሱ አንደበት:


<እኛ ሕንድ ወይም ሌላ አይደለንም
ኢትዮጵያውያን ነን>

ጥያቄ: ከአሜሪካኖች ጋር የነበረህ
ግንኙነት እንዴት ነበር?

መንግሥቱ- ቅድም እንዳልኩሽ
አሜሪካኖች ደካማ አይወዱም::
ድክመቱን ካዩ መጫወቻ ነው
የሚያደርጉት:: ዛሬ ጊዜና ሁኔታው
ተለውጦ ያሉትን ገዢዎች ከግራ ከቀኝ
እንደ ቴኒስ ኳስ ይጠልዙዋቸዋል እንጂ ሌላ ጊዜማ ይፈሩን ነበር::

እኛን <እንዲህ አድርጉ እንዲህ
አታድርጉ> ብለው ትዕዛዝ ሊሰጡን
እንደማይችሉ ስለሚያውቁ
አክብረውን ነበር
የሚኖሩት::<መጐብኝት ይቻላል
ወይ? ትፈቅዱልናላችሁ ወይ? ፕሬዝዳንቱን ለማነጋገር የሚመጣው
ማነው?> ብለው አስቀድመው
ይጠይቃሉ:: አንድ የመምሪያ ኋላፊ
ወይም ዳይሬክተር ከሆነ እኔ ጋር
አያቀርቡትም:: ፕሬዝዳንታችሁ
ወይም ሌላ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቢያንስ የሚንስትር ደረጃ እንኳን
የሌለው እንዴት የኛን ፕሬዝዳንት
ማነጋገር ይችላል ብለው ነው ከአየር
መንገድ የሚመልሷቸው::

ለምሳሌ ከዚህ ከአይሁዲው በፊት
የነበረው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር እሱም ራሱ አይሁዲ ነበር
<ፕሬዝዳንቱን ላነጋግር እፈልጋለሁ>
ይላል <ና> ይሉታል:: እሳቸውን
ማነጋገር እንደምችል ይረጋገጥልኝ እና ልምጣ> ይላል:: <አይ እንግዲህ
ከፈለክ ና:: ከመጣህ በኋላ አንተን
የማነጋገር ያለማነጋገር ጉዳይ የሳቸው
ውሳኔ ነው> የሚል መልስ
ይሰጡታል:: ሲመጣ <አሁን ምጽዋ
ጉብኝት እያደረጉ ነው የሉም ሲሉት <መንግስቱ ኋይለማርያም እኔን
ላለማነጋግር ሆን ብሎ ያደረገው ነው>
ብሎ ሌላም ሌላ ብዙ ተናገረ::
የውጭ ጉዳይ ሰዎች እነብርሃኑ ባየህ
ናቸው:: <አንተ የአሜሪካ ውጭ
ጉዳይ ሚንስትር ነህ ማነጋገር የምትችለው አቻህን ግፋ ቢል
ሌሎችን ሚኒስትሮች እንጂ
ፕሬዝዳንቱ ጋር ምን አንጠለጠለህ?
እኛ ለተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ
ኒውዮርክ ስንመጣ የናንተ ፕሬዝዳንት
ተቀብለው ያነጋግሩናል ወይ? ማን አስተናግዶን ያውቃል? አንተ ዘለህ
ይህን እንዴት ልጠይቅ ተደፋፈርክ?>
ይሉታል:: <እንዴ! እናንተ ማን
ሆናችሁ ነው እንደዚህ የምትሉኝ?
እኔኮ የትም ሀገር ሄጄ ጠቅላይ
ሚንስትሮችም ሆኑ ፕሬዝዳንቶች ያለችግር ተቀብለው ነው
የሚያናግሩኝ:: በቅርቡ የሕንድ
ጠቅላይ ሚንስትሩም ፕሬዝዳንቱም
ተቀብለውኛል> ሲል <እኛ ሕንድ
ወይም ሌላ አይደለንም
ኢትዮጵያውያን ነን> ብለው ይመልሱታል:: ከዚያ በኋላ ዝም
ብሎ ሄደና ኬኒያ ሲደርስ ጋዜጠኞችን
ሰብስቦ እኛን ሙልጭ አድርጐ
ተሳድቦ ወደ አገሩ ተመለሰ::> ገጽ
391-392

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s