ህወኃት በወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው፣

የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ተከዜን ተሻግሮ እስካሁን በሃይል የወሰዳቸው የጎንደር ወልቃይትና ፀገዴ ቦታወች ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ፀለምት፡ እና ከፀገዴ ከነበሩት ጠቅላላ 39 ቀበሌወች ውስጥ 25ቱን ቀበሌወች ወደ ትግራይ ወስዶ አንድ ወረዳ የመሰረተ ሲሆን ወደ አማራ ክልል ከፀገዴ የቀረው 14 ቀበሌ ብቻ ነው። አካባቢው በለምነቱ የታወቀና ድንግል መሬት ያለበት ሰፊ አካባቢ ሲሆን በብዛት የሚመረቱት የአዝርዕት አይነቶች ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ስኩኣር አገዳ፣ ፍራፍሬና አትክልት በስፋት ይመረታሉ። በዚሁ በወልቃይት ፀገዴ አካባቢ የሚገኙና ወደ ትግራይ የተወሰዱ ትላልቅ ከተሞች ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ/ ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞች ተወስደዋል።የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህንኑ የመስፋፋት ስስቱን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት አንገረብ ወንዝን በመጠቅለል የፀገዴ ቀሪ ቀበለወችን እና የታች አርማችሆ ለም መሬትን ለመውሰድ እየተዘጋጀ እንደሆነ ያካባቢው ጭብጦች ያስረዳሉ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: