ትውልደ ኢትዮጵያዊው፤ በኢራቅ የአክራሪ ንቅናቄ ትግል ውስጥ ተገደለ

የዓለም ዓቀፍ “እስልምና እምነት” ወኪል ነኝ በሚል ስያሜ ለራሱ የሠየመው “IS” የተባለውን ነውጠኛ አክራሪ የእስልምና ቡድንን የተቀላቀለ በዜግነት እንግሊዚያዊ የሆነ፣ ከኢትዮጵያ ወላጆች የሚወለድ የአስራ ሰባት አመት ወጣት በኢራቅ መገደሉን የቅርብ ዘመዶቹ ለሰንደቅ ገልፀዋል።

የሞቹ ወጣት አጎት የሆኑት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ለዝግጅት ክፍላችን ስለአሟሟቱ ሲገልጽ፤ “መሐመድ 17 ዓመት ወጣት ልጅ ነው። በጣም የምወደው ልጅ ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት እናቱ ወደ እኔ ደውላ መሐመድ በኢራቅ ሰማዕት ሆነ አለችኝ። የምትለኝ ነገር አልገባኝም። ጥሩ ነገር በወቅቱ አልተሰማኝም። ምን እያለችኝ እንደሆነ አጥብቄ ጠየቋት። ለእምነቱ ሲል በኢራቅ ተሰዋ አለችኝ። ከልቤ አዘንኩ። በማያውቀው ሀገር መውደቁ አስለቀሰኝ። እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። የምናገረው ጠፋብኝ። በሃይለቃል እናትየውን ምን እንዳልኳት እንኳን አላስታውስም። ብቻ ቆጨኝ። ነገሮች እንዲረዳ ለማድረግ ያደረገኩት ጥረት ባለመኖሩ አንገበገበኝ።” ብለዋል።

ወደ ኢራቅ መሄዱን ቤተሰቡ አያውቁም ነበር ወይ ብለን ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፤ “እናትየው ልጇ ወደጀርመን መሄዱን ነበር በወቅቱ የምታውቀው። እሱ ግን የሄደው ወደ ቱርክ ነበር። ሁሉም አክራሪ ሃይል የሚሰበሰበው ቱርክ ውስጥ ነው። በቱርክ ስልጠና ከወሰደ በኋላ ወደ ሶሪያ ግዛት እንዲገባ ይደረጋል። በሶሪያ አድርገው ወደ ኢራቅ ይሄዳሉ። ኢራቅ ሲደርሱ ከእስልምና አክራሪ ሃይሎች ጋር ይቀላቀላሉ። እዚያ ሲደርሱ ሁሉም እንቅስቀሴያቸው ሰማዕት ከመሆን ጋር አያይዘው ይሰብኳቸዋል። ወጣቶች በመሆናቸው ሞት አይፈሩም። ፍዳው ግን ለቤተሰብ ነው። የመሐመድ ሞት የእግር እሳት ነው የሆነብኝ። እናቱ እራሷ በዚህ አስተሳሰብ ተፅዕኖ ውስጥ መሆኗን የምትረዳው ልጄ ሰማዕት ሆነ ነው ያለችኝ። በድንፋታ ይህን የሞኝ ወሬሽን ወደዚያ አድርጊ። ቀሪ ልጆችሽን ብታስተምሪ ይሻላል። በቃ የተናገርኩትን አላውቅም” በማለት ሃዘናቸውን በምሬት” ገልጸውልናል።

አብዛኞቹ አክራሪ ወጣቶች ከእንግሊዝ ነው የሚሄዱት። እርሷም የእህት ልጅ ከእንግሊዝ ነው የሄደው። ለዚህ የተለየ ምክንያት አለ? ወይስ ከቤተሰቡ የሰሙት የተለየ ነገር አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ፤ “በርግጥ በእንግሊዝ እኔም እንደምሰማውም ከማነበውም ከቤተሰቡ የተረዳሁት የባሕል ልዩነቶች በስፋት የሚንጸባረቁበት ሀገር ነው። ከዚህም በላይ ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር በእንግሊዝ አለ። በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች በቀላሉ ልጆቹን በማሳመን ለአሸባሪነት ይመለምሏቸዋል። በአውሮፓም የተጋነነ እስልምናን የመፍራት ሁኔታዎች ስላሉ፣ በቀላሉ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታዮች ራሳቸው ከሌላው ሕብረተሰብ ይነጥላሉ። እነዚህ ሁኔታዎች አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች ይጠቀሙበታል። ይህን መሰል ሁኔታ ከቀጠለ ብዙ ወጣቶች በእነዚህ ሃይሎች ሰለባ ይሆናሉ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም በዚህ መንገድ እየተታለሉ ለአሸባሪ ሃይሎች መጠቀሚያ የሚሆኑ ወጣቶችን የምመክረው የእኔ የእህቴ ልጅ ለእናንተ ትምህርት ይሁን። እኔ ምንም ሳላግዘው፣ በአክራሪዎች እጅ ገብቶ በአጭሩ ለተቀጨው የእህቴ ልጅ ፈጣሪ ያስበው። በዚህ ወጣት ልጅ ነብስ ሌሎች ወጣቶች ለአክራሪ የሃይማኖት ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳትሆኑ አላህ ይርዳችሁ ብለዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: