ኢትዮ ቴሌኮም ሙስሊም ሰራተኞችን አስተዳደሮችን የሚያሸማቅቅ ህገ ደንብ አወጣ

የኢትዮ ቴሌኮም ስራተኞችና አስተዳደሮች ፂማቸውን እንዳያሳድጉ ተከለከለ!

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከወርሃ ሃምሌ 2003 ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ,ውስጥ ከነበረው አህባሽን በግዳጅ ከመጫን ሂደት ጀምሮ ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ተቋም ላይ የመረጣቸውን የመሳጅድ ኮሜቴዎችና ኢማሞችን በግዳጅ ከቦታቸው ላይ በማንሳት፣ የአህባሽን ሥልጠና አልወሰዳችሁም ተብለን ወደእስር ማጓዝ፣ ኢስላማዊ እውቀት መቅሰሚያዎች የሆኑትም መድረሳዎችንና የሂፍዝ ማዕከላትን መዝጋት፣ የዩኒቭርስቲ ተማሪ ወንድሞችን ፂማቹን ካልቆረጣችሁ፤ ሱሪያችሁን ካላሥረዘማችሁ አትማሩም በማለት ማሸማቀቅ እንዲሁም ሶላተችሁን አትስገዱ ማለት፣ሴት እህቶቻችን ኒቃብ ሂጃብ ጅልባብ እንዳይለብሱ መከልከል(የባህር ዳር ዩኒቭርስቲ ተማሪዎች ሶላትና ሂጃብ ተከልክለው በገፍ ማባረራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው) ፣ ሙስሥሊም ባለሥልጣናትን ከቦታቸው ማንሳት ወይንም ተፅዕኖ በማይፈጥሩበት ቦታ ካለ ፍላጎታቸው ማስሥቀመጥ፣ በትልልቅ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ,ሙሥሊም ወንድሞች ሱና እንዳይተገብሩ ማሸማቀቅና መከልከል፣ ሰላማዊ መብት ጠያቂዎችን በገፍ ማሰርና መግደል(የሃምሌ 11ዱ ጥቁር ሽብር የመንግሥትን አምባገነንነት በግልፅ ያየንበት ነው) እንዲሁም የመሳሰሉትን ይህ ነው የማይባል አስከፊ እኩይ ተግባራትን ካለአንዳች ርህራሄና እዝነት ከአንድ ሃገርን ይመራል ከሚባል መንግስት የማይጠበቅ የግፍ መዐት እንዳወረደብን ይታወቃል።

ይህ ኢሥላምንና ሙስሊሞችን የማክሰም ዘምቻ ካለፈው ወርሃ ሃምሌ 2003 ዐ.ል ጀምሮ ሙስሊም ሙህራንን፣ የፕሪፓራቶሪ(Preparatory) ፤ የሃይስኩል(Highschool)፣ የዩኒቨርስቲ(universities) ተማሪዎችን፣ ዳዒዎችን፣ ኢማሞችና ሙዓዚኖችን ኢላማ በማድረግ አሥከፊና አስነዋሪ እርምጃዎችን ወስዷል እየወሰውደም ይገኛል።

ምንጮቻችን እንደገለፁት ያለፈው ሳምንት አመታዊ የስራ ክንውኖችንና ቀጣይ የማሻሻያ ግምገማና ውይይት የመንግስት ትልቁ ተቋም የሆነው የኢትዮጲያ ቴሌ ኮሚኒኬሽን ኮርፔሬሽን(ኢትዮ ቴሌኮም) ሰራተኞችና ጨምሮ የመስሪያ ቤቱ ትልልቅ ባለስልጣናት የተሳተፉበት ስብሰባ መካሄዱን የገለፁ ሲሆን በስብሰባውም ላይ በቴሌኮሙ ቀጣይ መሻሻልና መደራጀት ያለባቸው አሰራሮች ከስራተኞቹ የቀረቡ ሲሆን መሻሻል እንዳላባቸውና ከውጪ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማምጣት የተቀላጠፈ አስራር በያዝነው አዲስ አመት አሻሽለን እንቀጥላለን በማለት ውይይቱ ተጠናቋል።

ይሁንና አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪና የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በአ/ቶ ደብረ ፂዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የኢትዮጲያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን(ኢትዮ ቴሌኮም) ካለፈው ከተቋጨውና በውይይታቸው ላይ ከተነሳው አጀንዳ ውጪ ሙስሊም ሰራተኞችን በግልፅ የሚያሸማቅቅና በግልፅ ሙስሊም የቴሌኮሙን ሰራተኞችን ኢላማ ያደረገ ህገ ደንብ እንደወጣ የአዛን አንቲ-አህባሽ የመረጃ መረብ ምንጮች ገልፀዋል።

በህገ ደንቡ ላይ ማንኛውም የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችና አስተዳደር ፂሙን ማሳደግ እንደማይችል፣ ሱሪውን ማሳጠር እንደማይችል፣ ለሴቶች ,ደግሞ አባያ፤ጅልባብ፤ኒቃብ፣ አባያ መልበስ እንደማይችሉ፤ጉርድ ,ቀሚስ ና ሸሚዝ እንዲያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሙስሊሞችን ብቻ አላማ ያላደረገ ለማስመሰል በደንቡ ላይ ፀጉር ማሳደግ፣ ፀጉር መፈረዝ፣ ሲኪኒ ሱሪ መልበስ እንደማይችል …ወ.ዘ.ተ እንደተገለፀ ታውቋል።

የወጣው ህገ ደንብም ከጥቅምት ወር 2007 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ምንጮች አያይዘው ዘግበዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s