እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል

• ‹‹ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን፡፡›› የብአዴን አመራሮች

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጾአል፡፡

በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጾአል፡፡

ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት ገልጾአል፡፡

ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲና አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል፡፡ በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን›› እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል፡፡

የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

Advertisements

በህዳሴው ግድብ ላይ ጥቃት ለማድረስ ያቀዱ ስድስት ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

በህዳሴው ግድብ ላይ ጥቃት ለማድረስ ያቀዱ ስድስት ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

በኤርትራ የፖለቲካና የጦርነት ስልጠና የወሰዱ ናቸው ግለሰቦቹ፡፡

ግለሰቦቹ ስለጠናውን ከወሰዱ በኋላ በግድቡ ላይ ጥቃት የማድረስ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በሱዳን ድንበር በኩል ሲያቋርጡ በደህንነት ጠባቂዎች መያዛቸው ተገልጿል ሲል የዘገበው ሆርን አፌርስ የዜና ምንጭ ነው፡፡

ጥቃቱን ለማድረስ በኤርትራ የሰለጠኑት ግለሰቦች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ማህበረሰብ የወጡ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

http://goo.gl/9Ou0WI

Featured image

የስንፈተ ወሲብ መፍትሄዎች ለወንዶች

 (Reactive Dysfunction & Premature Ejaculation)

Posted by on October 10, 2013

Premature-Ejaculation

ተሰባስበን በመጠጣት ላይ እያለን እንዳጋጣሚ አንዱ ጓደኛችን ቪያግራ ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መድኃኒት አነሳን፡፡ እሱ እንደነገረን ግን የስንፈተ ወሲብ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በሞቀ ስሜት ለመቆየት የሚያስችል እና በቅርብ ጓደኛው ከዱባይ እንዳመጣለት ነገረን፡፡ የተወሰኑት በእረፍትና በድፍረት መሀከል ሆነው እስኪ እንሞክረው ሲሉ ተስማሙ፡፡ እኔና አንዱ ጓደኛችን በድምፅ ተአቅቦ ዝም ብለን ማዳመጥ ቀጠልን፡፡ እርግጥ አልፎ አልፎ ከባለቤቴ ጋር ወሲብ ለመፈፀም ስፈልግ ስሜቴ ስለማይነቃቃ ባለቤቴ ላይ መከፋት አያለሁ፡፡ እናም እንዲህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር እንደጓደኞቼ ምን አለ ብጠቀም ብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ግን ስጋቴ ከዛ በኋላስ ምን ሁኔታ ውስጥ እገኛለሁ ብዬ ሳስብ ይጨንቀኛል፡፡ ታዲያ ለዚህ ብዬ ባለሙያዎችን ለማማከር ወደ ህክምና ብሄድ ቅብጠት ይሆንብኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ልጠቀም አልጠቀም በሚል ውዝግብ ለመውጣት ሁሉንም ለመርሳት ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን መድኃኒቱን ከሌላ ሰው እጅ በማግኘቴ ገዝቼ አስቀምጬዋለሁ፡፡ እንደው ምን አልባት ቢያስፈልግ ብዬ፡፡ ሲል ስሙን እንዳልጠቅስ ከነማስጠንቀቂያ የነገረኝ ጓደኛዬ ያነሳልኝን ጨዋታ ተመርኩዤ በዚህና መሰል የስንፈተ ወሲብና አማራጭ መድኃኒቶች ዙሪያ ባለሙያ አነጋግሬ ይዤላችሁ ቀረብኩ፡፡ ችግሩ በአበባ ወጣቶች ላይ መንሰራፋቱን ከተለያዩ ሰዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡ እናስ ህክምናው ምን መልስ አለው፡፡ ዶ/ር ድጋፌ ፀጋዬ የቆዳና የአባላዘር ስፔሻሊስት ናቸው፡፡ ከስንፈተ ወሲብ በመነሳት እንዲህ ያስረዱናል፡፡

 peremachureበወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስት መልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳት ችግር (Reactive dysfunction) ወይም የወሲብ ስንፈት እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስ የዘር ፈሳሽ ማውጣት (premature ejaculation) ሶስተኛው የወሲብ ስሜት አልባነት ናቸው፡፡

የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግር ያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያጠቃም በተደጋጋሚ ወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመት በላይ በሆኑት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም ሪፖርት ሊያደርጉ ችለዋል፡፡

ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነት ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና (Phylogenic) ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኦርጋኒክ (ምክንያታዊ) የሆኑ የተለያዩ በሽታዎች በሚፈጥሩት ተፅዕኖ ይከሰታል፡፡ ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረት በሚኖርበት ጊዜ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብ ያጋልጡናል፡፡ ሌላው የአካል ድካም እና መዛል ነው፡፡ ለምሳሌ አካሉ በብዙ ስራ ሲንቀሳቀስ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅት የብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡ ብልት እርቀት ደረጃ ሳይደርስ አስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ምክንያት የሀሳቦችን መደራረብ በመኖራቸው ነው፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከት ከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነ ስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነ ስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳ በአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከል አለመግባባት /ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱም ወገን ይቀንሳል፡፡ በቀጥታ ከአዕምሮ ጋር የሚያያይዘው የግብረ ስጋ ግንኙነት ስነ-ልቦናና አካላዊ ዝግጁነት ጅማሪ አይምሮ ውስጥ በሚፈጠር ኬሚካሎች አማካይነት ነው፡፡ የአንድሮጂን ኬሚካል መመረት ወንዶች ላይ ብዛት የደም ፍሰቱ ወደ ብልት እንዲሆን በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው ምክንያቶች ይህን ኬሚካላዊ የዝግጁነት ቅመም እንዳይፈጠር ስለሚያደርጉ የፓርኖግራፊ ፊልሞች በሚፈጥሩት፣ በአደጋ (ግጭት) ጫና፣ በሃዘን፣ በድካም መካከል ስንፈተ ወሲብ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም ነው ብልት የመነሳት ችግር የሚያጋጥመው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ኦርጋኒክ የሚባለው ሲሆን የተለያዩ ህመሞችን ተከትሎ የሚመጣ የወሲብ ችግር ሲሆን ስኳር፣ ደም ግፊትና የአባላዘር በሽታዎች ሲያጠቁን ነው፡፡ ሌላው የተለያዩ አደገኛ መድኃኒቶች አልኮልና ጫት የደም ዝውውርን የሚቀንሱ ናቸው፡፡ በግንኙነት ወቅት ብልት እንዲነሳ ካስፈለገ ከፍተኛ የደም ዝውውር ሊኖር ይገባል፡፡ በቂ የሆነ የነርቭ መነቃቃትም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ነገሮች የሚያስከትሉት ጫና ደግሞ በወሲብ የመነቃቃትና ትክክለኛውን ኡደት ጠብቆ በሚጠበቀው ደረጃ እርካታ ላይ ለመድረስ እንዳይችሉ እንቅፋት ይሆናል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉን ህክምናዊ መፍትሄዎች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ስንመለከት በቅድሚያ ወሲባዊ ህይወት እንደ ምስጢር በየሰው አዕምሮ ውስጥ በመቀበሩ ችግሮችን አውጥቶ ከህክምና ባለሙያዎች እና ከትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛ ጋር ለመወያየት አለመቻል በራሱ ችግሩን የሚያባብሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ከህክምናው ጋር የተገናኙትም በትክክል ህክምና ተከታትለው ሲያጠናቅቁ አይታዩም፡፡ በመሆኑም በቀላሉ መፍትሄ ላያገኙ ከሚችሉበት አጋጣሚ በመራቅ ለተለያዩ አላሰፈላጊ የጊዜና ገንዘብ ብክነቶች ይዳረጋሉ፡፡

በመሆኑም መፍትሄው የመጀመሪያው እርምጃ የችግሩን መነሻ ምክንያትን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ እንደመንስኤው የተለያዩ ህክምናዎች እንዲሰጡበት ያደርጋል፡፡ ከስነ-ልቦና ጋር የተያያዘ ከሆነ ያለመድኃኒት ሊስተካከል ይችላል፡፡ ያለውን ችግር ማለትም አካላዊና አዕምሮአዊ ሁኔታ የስነ-ልቦና ድጋፍ በማግኘት በማስተካከል ሊቀረፍ ይችላል፡፡ ከተለያዩ ህመሞች የሚነሳው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከመቆጣጠርና ከመከላከል ባሻገር መድኃኒቶችን ለደም የሚገባውን የወሲብ ስሜት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ፡፡ በዚህ ውስጥ አልፈን መፍትሄ ካልተገኘ የመጨረሻው አማራጭ ረዳት መድኃኒቶችን ማካተት ይሆናል፡፡

እነዚህ መድኃኒቶች ያላቸው ጥቅም ምንድን ነው ካልን የደም ዝውውር በመጨመር ነርቮች እንዲነቃቁ የወንዱ ብልት አካባቢ ያሉት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና ብልት እንዲጠነክር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ መድኃኒቱም በህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ መሰረት በጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም አይነትና መጠኑ ሊያውቅ የሚችለው በህክምናው ዘርፍ በቂ ትምህርትና ልምድ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ተያይዘው ለሚመጡ ተጓዳኝ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ተጠንተው ቅድመ እና ድህረ ጥንቃቄ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ችግሩ እንዲቀረፍ 50 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ከችግሩ አይነትና መጠን ተነስተን ነው መድኃኒቶቹን የምናዘው፡፡

መድኃኒቶች ያሏቸውን ጥቅም ያህል ብዙ ጉዳቶችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው የባለሙያ ድጋፍ አስፈላጊነት ሁኔታዎችን በማገነዛብ መድኃኒቶችን ማዘዝ ውጤታቸውንም መከታተል ከተቻለ መድኃኒቱ ያለምንም ጉዳት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ይረዳዋል፡፡

መድኃኒቱ መታዘዝ ያለበትን ወቅት በተመለከተ ምክንያቱ ታውቆ አማራጭ መፍትሄዎች ታይተው ግድ የሚሉ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ነው፡፡ የመድኃኒቱ መጠን እና አይነት መቼስ መውሰድ አለበት? እነማንናቸው መድኃኒቱን መውሰድ የሚችሉት? እነማንስ መድኃኒቱንሲወስዱ ችግሮች ይገጥማቸዋል? የሚለውን የሚወስነው ባለሙያው ነው፡፡

premachሰዎች ከተለያዩ ምንጮች ካገኟቸው መረጃዎች ተነስተው መድኃኒቶችን ያለህክምና ትዕዛዝ ይወስዳሉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ለችግሩ ትክክለኛ መፍትሄ ሊሰጥ ወደሚችለው ባለሙያ ለመሄድ ያለው ተነሳሽነት በጣም ዝቅተኛ መሆን፣ የወሲብ ምስጢራዊነት እሳቤ፣ የመድኃኒቶቹን የጎንዮሽ ችግር ያለመረዳት፤ የጓደኛና የተለያዩ የወሲብ ትዕይንቶች ከሚያስከትሉት ጫና የተነሳ ነው፡፡ ችግሩ ሳይኖር መድኃኒቶችን አፈላልጎ መጠቀም የመቻል አቅምና ድፍረት በተጨማሪ ህገ-ወጥ የመድኃኒት ዝውውር መኖሩ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ለምሳሌ ቪያግራ ተሰኘውን መድኃኒት በተለያየ መልኩ ማግኘት የቻሉ ሰዎች ዝም ብለው ቢጠቀሙበት ምን ያስከትላል ስንል የልብ ድካም ያለባቸው (አርቴፊሻል መሳሪያዎች በልባቸው የተገጠመላቸው ሰዎች) ችግር ይገጠማቸዋል፡፡ መድኃኒቶቹ በዚህ ሁኔታ ከጥቅም ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል፡፡

በተጨማሪም ከልክ ያለፈ የብልት መነቃቃት ሳቢያ ብልት ቆሞ ላይመለስ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ይህም Persistence stimulation ያስከትላል፡፡ ሌላው በግንኙነት ወቅት ብልት በጣም ከመወጣጠሩ የተነሳ የብልት ዘንግ ስብራት ሊያጋጥም የሚችላቸው ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡ አንድም ጊዜያዊ ከፍተኛ ህመም፡፡ በተጨማሪም የልብ ስራን የማዛባት ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡

የስንፈተ ወሲብ መድኃኒቶቹን ማግኘት ስለተቻለ ብቻ መጠቀሙ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ብዙ ጊዜ መድኃኒቱ እንደ ችግሩ ሁኔታ ታይቶ በቀን አንዴ ግንኙነት ከማድረጊያ ጊዜ አንድ ሰዓት ቀድሞ እንዲወሰድ የሚታዘዝ ሲሆን በተደጋጋሚ እንዲወሰድ አይመከርም፡፡

መድኃኒቱን ደጋግሞ መውሰድ አስቀድመን የጠቀስናቸውን ችግሮችን ማባባስ ያስከትላል፡፡ በተለምዶ የወንዶች ብልት ከተነሳ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ቀድሞ ቦታው ይመለሳል፡፡ ለረጅም ሰዓት ተነስቶ በሚቆይበት ወቅት እጅግ በጣም ከፍተኛ ህመም አለው፡፡ መልሶ ግንኙነት ማድረግ በሚያስፈልግበት ጊዜም ሊያስቸግር ይችላል፡፡

እንደ ቪያግራ ያሉ መድኃኒቶችን መጠቀም የጀመረ ሰው የጥገኝነት ባህሪ ስለሚዋሃደው ያለው በራስ መተማመን ይቀንሳል፡፡ ያለመድኃኒቱ በተፈጥሮአዊ መንገድ ለወሲብ መዘጋጀት እና መደሰትም ያቅተዋል፡፡ የቪያግራ መድኃኒት በኪኒን መልክ የሚሰጥ ሲሆን አልፎም በመርፌ መልክ ወንድነትን የሚያላብሰው የቴስቴስትሮን ሆርሞን በጊዜ ሂደት ሲቀንስ ቅመም አመንጭውን ክፍል ለማነቃቃት (መጠኑን ለመጨመር) የሚያስችል በሳምንት አንድ መርፌ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ስንፈተ ወሲብ ያስከተለው የቴስቴስትሮን ማነስ፣ የስነ-ልቦና ጫና አካላዊ ድካም ወዘተ… መንስኤዎች ውስጥ የትኛው እንደሆነ ታውቆ መድኃኒቶች ይመረጣሉ፡፡

አብዛኛው ስንፈተ ወሲብ ችግሮች ባህሪን ከማስተካከል፣ ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ እና ምክር በመስጠት ያለመድኃኒት ሊታከሙ የሚችሉ ናቸው፡፡ ህክምና ቦታ መጥተው ፈራ ተባ እያሉ የመናገር ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ ይህ ተወግዶ ግልፅነት ከዳበረ ችግሩ እንዲቀረፍ ይረዳል፡፡ በወጣቶች በኩል ለዚህ ችግር የሚጋለጡበት ዋነኛ ምክንያት በሱስ መጠመድ ሲሆን በተለይም ለረጅም ጊዜ ጫት መቃም እና በብዛት አልኮል የሚወስዱ ከሆነ ለስንፈተ ወሲብ ይጋለጣሉ፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚኖር ከግብረ ስጋ ግንኙነት ለስንፈተ ወሲብ ያጋልጣል፡፡ በደንብ ሳይተዋወቁ ስሜታዊ ወሲባዊ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ሰዎች በሚያድርባቸው ስነ-ልቦና ጫና የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡

እኛ አገር ባይኖርም በባለትዳሮች መሀከል የሚደረግ የወሲብ ህክምና በተለያዩ ሀገሮች የሚሰጥ ሲሆን ከትዳር አጋር ጋር በሚያጋጥም የወሲብ አለመጣጣም ችግሮችን በማጥናት መፍትሄ ማስቀመጥ የሚቻልበት ሂደት ነው፡፡ በወሲብ ህይወት ውስጥ ዝግጁነት እና ግልፅነት ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለ ወሲብ ከትዳር አጋር (ፍቅረኛ) ጋር በግልፅ በማውራት ለችግሮቹ መፍትሄ ለመፈለግ ይረዳል፡፡ በዚህ ሳቢያ የሚደርስ የትዳር መፍረሶችን መታደግ ይቻላል፡፡ ተገቢውን ህክምና ማግኘት እና በተለይም ቤተሰባዊ መረዳዳት እና በወሲብ ወቅት ማዘጋጀት፣ እራስን የተረጋጋ፣ ፍቅር የተሞላበት እና መተማመን የሰፈነበት ወሲብ ሙሉ ደስታን ያጎናፅፋል፡፡

ቪያግራን ወንዶች ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ሲጠቀሙበት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝንም የታወቀ ሲሆን ይህ መድኃኒት ለሴቶች ጥቅም ስለማይኖረው በድፍረት እና ባለማወቅ የወሲብ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለው ሴቶች እንዳይቀጠሙበት እናስጠነቅቃለን፡፡

መድኃኒቶች ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ጥራታቸው ያልተፈተነ፣ የማዳን አቅማቸው፣ የጎንዮሽ ጉዳታቸው፣ የአወሳሰድ መጠናቸውና ልዩ ጥቅም የሚያስገኝባቸው ችግራዊ መንስኤዎች ስለማይታወቁ ያለሐኪም ትዕዛዝ መውሰዱ ለከፋ ችግር ያጋልጣሉና የጥንቃቄ እርምጃው እየተስተዋለ ሊሆን ይገባዋል፡፡

– See more at: http://www.tenaadam.com/amharic/archives/1449#sthash.5mjlGI4E.dpuf

በሽሬ ከተማ ከቄራ ውጭ የታረዱ የስምንት በሬዎች ሥጋ ተቃጠለ

 

Featured image

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ከቄራ ውጭ የታረዱ የስምንት በሬዎች ሥጋ እንዲቃጠል መደረጉን የከተማው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የጤና ቁጥጥር ባለሙያ ወይዘሮ ግድይ ገብረክርስቶስ በሰጡት አስተያየት ከቄራ ውጭ ንጽህናው ባልተጠበቀና ተገቢ ምርመራ ሳይደረግላቸው የታረዱ የስምንት በሬዎች ሥጋ እንዲቃጠል መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ያልተመረመረና ንጽህናውን ባልጠበቀ ቦታ የታረደ ሥጋ በመመገብ ሊደርስ ከሚችለው የጤና ችግር ህብረተሰቡን መታደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ሥጋ ከሚሸጡት መካከል አቶ በርኽ ሓለፎም በሰጡት አስተያየት በከተማው ያለው ቄራ የሚሰጠው አገልግሎት ውሱንና የተሟላ ባለመሆኑ ከቄራው ውጭ ለማረድ ተገደናል ብለዋል።

ሜንጭ እዜአ

የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ለስም የተቋቋመ አይደለም – የውጭ ጉዳይ ሚስቴር

Featured image

የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ለስም የተቋቋመ አይደለም – የውጭ ጉዳይ ሚስቴር

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አል ሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ይችላል ማለቱን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ በተገኙበት በዚሁ መግለጫ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚነስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳር ታዮ አጽቀስላሴ አሜሪካ ለሰጠችው ማስጠንቀቂያ ምሰጋናቸውን አቅርበው ‹‹የኢትየጵያ የደህንነት ተቋም ለስም ብቻ አልተቋቋመም ፤ የአልሸባብንም ሆነ የሌሎች አሸባሪ ሃይሎችን እንቅስቃሴ በተገቢው መንገድ ይከታተላል፡፡ በመሆኑን አናንተ አሜሪካኖችም ሆናቹ ሌሎች የውጭ ዜጎች ያለስጋት ተንቀሳቀሱ ›› የሚል ምክር አዘል አሰተያየት ሰንዝረዋል፡፡

በሽብርተኝነት ዙሪያ በቂ ልምድ አለን ያሉት ዳይሬክተሩ የአሜሪካ መንግስት ጥቆማን በበጎ መልኩ እንደሚመለከቱት እና ጠቃሚ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አመባሳደር ፓትሪሺያ የመግለጫው አንድ አካል ባይሆኑም ‹‹የአሜሪካ መንግስት መሰል ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስተላልፍ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት ሀገር ዜጎችን ለጭንቀት እና ለፍራቻ በማያጋልጥ መልኩ ለምን አይለቅም? ለምንስ ማስጠንቀቂያው የአሜሪካ ዜጎችን እና ውጭ ዜጎችን ብቻ እንዲጠነቀቁ ይመክራል? አደጋው በሁሉም ላይ ነውና›› የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

አምባሳደሯ ማስጠንቀቂያው በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የተለቀቀ መሆኑን አስታውሰው በጉዳዩ ላይ የሚሉት ተጨማሪ ነገር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አመባሳደር ፓትሪሺያ የመግለጫው አንድ አካል ባይሆኑም ‹‹የአሜሪካ መንግስት መሰል ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስተላልፍ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት ሀገር ዜጎችን ለጭንቀት እና ለፍራቻ በማያጋልጥ መልኩ ለምን አይለቅም? ለምንስ ማስጠንቀቂያው የአሜሪካ ዜጎችን እና ውጭ ዜጎችን ብቻ እንዲጠነቀቁ ይመክራል? አደጋው በሁሉም ላይ ነውና›› የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

አምባሳደሯ ማስጠንቀቂያው በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የተለቀቀ መሆኑን አስታውሰው በጉዳዩ ላይ የሚሉት ተጨማሪ ነገር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡

ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር ለቴክሳስ ግዛት ሴናተርነት ሊወዳደር ነው

እ.ኤ.አ በ1964 የተወለደው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ምሁር ሞሃመድ ጣሂሮ ለቴክሳስ ግዛት ሴናተርነት ሊወዳደር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምሁሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪውን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ‹‹ በወቅቱ በነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት›› ምክንያት እ.ኤ.አ በ989 በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ እንደገባ ማስረጃዎ ይጠቁማሉ፡፡

የፕሮፌሰር ሞሀመድ ጣሂሮን መረጃዎች ይመልከቱ

http://goo.gl/s52fEc

Featured image