የፓርቲዎቹ አባላት ጠበቃ ደረሰብኝ ባሉት ጫና ለጊዜው ሥራቸውን ማቆማቸውን አስታወቁ

Freedom4Ethiopian

በሕገመንግስቱ መሠረት ለደንበኞቼ አገልግሎት መስጠት አልቻልኩም፤ ከፍርድ ቤትና ከፖሊስም ማስፈራሪያ ደርሶብኛል ያሉት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና ፓርቲ አባላት ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። ደንበኞቼ የምርመራ ቃላቸውን ለፖሊስ ከመስጠታቸው በፊት ላገኛቸው ሲገባ ይህ አልተደረገም ያሉት ጠበቃው፤ የጊዜ ቀጠሮው ችሎት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለቀጣዩ አንድ ወር ደንበኞቻቸውን እንደማያገኙና ሕግን ባልጠበቀ መንገድ ለሚከናወን ተግባር የፕሮፓጋንዳ ሽፋን መሆን እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል።
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለአንድነት ፓርቲ አባላቱ ለሀብታሙ አያሌውና ለዳንኤል ሺበሺ፤ ለአረናው አብርሃ ደስታ እና ለሰማያዊ ፓርቲው የሽዋስ አሰፋ ጠበቃ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኙ የነበሩ ሲሆን፤ ደረሰብኝ ባሉት ጫና እና ኢ-ሕገመንግስታዊ አሰራር ምክንያት ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለጊዜውም ቢሆን ማቋረጣቸውን ለፓርቲዎቹ አመራሮች መግለፃቸውን አስረድተዋል። ይህም በመሆኑ ሦስቱ ፓርቲዎች (ማለትም አንድነት፣ ዓረና እና ሰማያዊ) በእስረኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት በተመለከተ ዛሬ መስከረም 21 ቀን 2007 ዓ.ም በአንድነት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንደማንኛውም ጠበቃ ደንበኞቼን ማግኘት ቢኖርብኝም፤ ላገኛቸው አልቻልኩም፤ በፍርድ ቤት የምናቀርባቸው አቤቱታዎች እና ስሞታዎች በሙሉ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ ይደረጉብናል፣ ይባስ ብሎም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር…

View original post 160 more words

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s