እንኳን ለጨርቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

Featured imageFeatured image

እንዲያው ለምዶብኝ ፋይዳ ባለው እና ፋይዳ ቢስ በሆነው ሁሉ እንደ ሀበሻ “እንኳን በሰላም አደረሳችሁ” ማለት እወዳለሁ፣ እና አሁንም በድጋሜ “እንኳን ለጨርቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ”።
ለምን “ጨርቅ” አልከዉ ማለታቹህ አይቀሬ ነውና የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ተብየው የዜናዊ ልጅ እንዳለዉ ” ጨርቅ” ነው። እኔን እና የዜናዊ ልጅን የሚያመሳስለን “ጨርቅ” ማለታችን ሲሆን ልዩነታችን ደሞ የዜናዊ ልጅ “ጨርቅ” ያለዉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን ሲሆን እኔ ደሞ “ጨርቅ” ያልኩት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን ሳይሆን የወያኔን ሰንደቅ አላማን ነዉ (ከመሀሉ አምባሻ ያለዉ ባንዴራ)። ለምን አምባሻ እንዳደረጉበት ዩሱፍ ሞሐመድ እንደ ማከተለዉ ተርኮታል እና እንሆ ጀባ ብየዎትለዉ…………………

“”የሰይጣናዊ አመለካከት ማለት የተለያዩ የፖለቲካ ዘይቤና ፍልስፍና ያላቸው ሰዎች ባንድ ላይ በመሆን የሰይጣን አድናቂ እና በሰይጣን ምልክት ሁላቸውም አንድ ሆነው ሲስተዋሉ ነው።በ1990 እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የሰይጣናውያን ቁጥር 50ሽ እንደነበር ምንጮች ይናገራሉ።ምናልባትም ይላሉ ሌሎች ምንጮች በአለም ላይ በ100ሽዎች የሚቆጠሩ ሰይጣናውያን እንደነበሩ ያትታሉ በተለይም ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ወድህ በምዕራብ አውሮፓ በስልጣኔ ብቅ ብቅ ማለት ጋር ተያይዞ የተከሰተ እንደነበር አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ።ይህ ዘመን የምክንያት ዘመን ይሉታል,ማየት ብቻ ማመን የነበረበት ዘመን ነበር።የጀብደኝነት ግጥም ገጣሚው እንግሊዛዊው ጆን ሚልቶን ፓራድዝ ሎስት በሚለው መጽሃፉ ላይ አዳምና ሄዋን በኤደን/ገነት በሰላም ከፈጣሪ ጋር እየኖሩ ሳለ መልአኩ ሰይጣን መጥቶ ለፈተና ዳረጋቸው ከዛውም ከገነት ተባረሩ በዚሁ መጽሃፉ ፌል ኦፍ ማን በሚለው የታሪክ ስራው ጆን ሚልቶን።ሌተርስ ፍሮም ዘ ኤርዝ የተሰኘው የማርክ
ትዎይን ስራም ሳታኒዝም እንድስፋፋ አስተዋጽኦ እንደነበረው ይነገራል።በይፋ በ1948 በኦሃዮ ሄርበርት አርቱር ስላኔ ኦፋይት ኩልተስ ሳታናስ የሚባል ማህበር መሰረተ።በ1966 የሰይጣን ማምለኪያ ቦታ ዘ ቸርች ኦፍ ሳታን ተብሎ ተከፈተ።በ1960 ሰይጣናውያን ለብዙ ተከፋፍለው እንደነበር ይነገራል በዋነኝነት ግን ለሁለት በአምላክ መኖርና አለመኖር በሚሉት ተከፍለው እንደነበር ይነገራል።በእንግሊዝ የታጠቁ የንጉሳውያን ወታደር ህይሎች ሰይጣናዊነት ተፈቅዷል።የሰይጣናውያን ቤተ አማልዕክት እምትጠቀምበት ህጋዊ አርማ ላቬያን ሳታኒዝም ትባላለች።አሁን ነገሩ ወድህ ነው የአገራች ኢትዮጵያ መለያ ክብር የሆነው ሰንደቃችን መሃል አንጀቱ ላይ ተለጥፎ እምናየው የኮከቡ አርማ የሰይጣናውያን አምላኪዎች ህጋዊ በቤተ አማልእክታቸው የሚጠቀሙበት መለያቸው እንደሆነ ያስረዳናል።እንደው ጉልቻ ቢቀያየር መች ወጥ ያጣፍጥና ይችን የመሰለች አረንጓደ ቢጫ ቀይ ሰንደቃችንን ባንለጣጥፍባትና የሃይማኖትና የገድል ተምሳሌት የሰው ልጅ መገኛ የአኩሪ ድል ባለቤት የነበረችውን አገራችንን ምነው በንደዚህ አይነቱ ምልክት ባንዎክላት።ስንዘምርለት ትንፋሻችን የሚያጥርለት ሰንደቃችንን በሰይጣን አርማ ??? ፍርዱን ለናንተው”””

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s