በሊባኖስ የብሪታኒያ አምባሳደር ከኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ጋር ቦታ ተቀያይረው አምባሳደሩ የቃል ኪዳንን የምግብ ማብሰል ስራ ሲሰሩ ዋሉ…..

በሊባኖስ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆኑት ቶም ፍሌቸር ከኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ቃል ኪዳን ጋር ቦታ ተቀያይረው አምባሳደሩ የቃል ኪዳንን የምግብ ማብሰል ስራ ሲሰሩ ዋሉ…..

በሊባኖስ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው በሚሰሩ ኢትዮጵያውያንና የሌሎችም ሀገራት ዜጎች ላይ የሚደርሰው በደል እና ግፍ በመላው ዓለም የታወቀ ሆኗል፡፡ በትላንትናው ዕለት ብቻ በአንዲት በሊባኖስ በምትገኝ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የደረሰውን አደገኛ ውንጀላ እና በሳዑዲ ራሷን ስላጠፋችው ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በሊባኖስ ሰብዓዊ ክብራቸው ተረግጦ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን የሚከራከር ወገን በጠፋበት በሊባኖስ የብሪታኒያው አምባሳደር ያደረጉት ተግባር የሚደነቅና የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡

አምባሳደሩ በትዊተራቸው ላይ ባስታወቁት እና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በተለቀቀው ንግግርና ምስላቸው ላይ እንደታየው “ሰብዓዊ ክብራቸው እየተጣሰ ላለው የቤት ሰራተኞች ክብራቸውንና ሰብዓዊ መብታቸውን ማክበር እንደሚገባ ለማሳየት” በሚል ቃልኪዳን የተባለችውን ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ስራ ወስደው ሲሰሩ ታይተዋል፡፡

አምባሳደሩ በቃል ኪዳን ታዛቢነት በብሪታኒያ ኤምባሲ ውስጥ ቤት አጽድተው፣ እቃ አጥበው፣ ምግብ ሰርተው አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ ቃል ኪዳንን ይዘው ወደ ሊባኖስ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር በማምራት የቤት ሰራተኞችን መብት በማክበር እና ክብራቸውን በመጠበቅ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

http://goo.gl/rPdEmS

Featured image

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s