የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ለስም የተቋቋመ አይደለም – የውጭ ጉዳይ ሚስቴር

Featured image

የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ለስም የተቋቋመ አይደለም – የውጭ ጉዳይ ሚስቴር

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አል ሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ይችላል ማለቱን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ በተገኙበት በዚሁ መግለጫ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚነስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳር ታዮ አጽቀስላሴ አሜሪካ ለሰጠችው ማስጠንቀቂያ ምሰጋናቸውን አቅርበው ‹‹የኢትየጵያ የደህንነት ተቋም ለስም ብቻ አልተቋቋመም ፤ የአልሸባብንም ሆነ የሌሎች አሸባሪ ሃይሎችን እንቅስቃሴ በተገቢው መንገድ ይከታተላል፡፡ በመሆኑን አናንተ አሜሪካኖችም ሆናቹ ሌሎች የውጭ ዜጎች ያለስጋት ተንቀሳቀሱ ›› የሚል ምክር አዘል አሰተያየት ሰንዝረዋል፡፡

በሽብርተኝነት ዙሪያ በቂ ልምድ አለን ያሉት ዳይሬክተሩ የአሜሪካ መንግስት ጥቆማን በበጎ መልኩ እንደሚመለከቱት እና ጠቃሚ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አመባሳደር ፓትሪሺያ የመግለጫው አንድ አካል ባይሆኑም ‹‹የአሜሪካ መንግስት መሰል ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስተላልፍ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት ሀገር ዜጎችን ለጭንቀት እና ለፍራቻ በማያጋልጥ መልኩ ለምን አይለቅም? ለምንስ ማስጠንቀቂያው የአሜሪካ ዜጎችን እና ውጭ ዜጎችን ብቻ እንዲጠነቀቁ ይመክራል? አደጋው በሁሉም ላይ ነውና›› የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

አምባሳደሯ ማስጠንቀቂያው በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የተለቀቀ መሆኑን አስታውሰው በጉዳዩ ላይ የሚሉት ተጨማሪ ነገር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አመባሳደር ፓትሪሺያ የመግለጫው አንድ አካል ባይሆኑም ‹‹የአሜሪካ መንግስት መሰል ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስተላልፍ ማስጠንቀቂያ የተላለፈበት ሀገር ዜጎችን ለጭንቀት እና ለፍራቻ በማያጋልጥ መልኩ ለምን አይለቅም? ለምንስ ማስጠንቀቂያው የአሜሪካ ዜጎችን እና ውጭ ዜጎችን ብቻ እንዲጠነቀቁ ይመክራል? አደጋው በሁሉም ላይ ነውና›› የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

አምባሳደሯ ማስጠንቀቂያው በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የተለቀቀ መሆኑን አስታውሰው በጉዳዩ ላይ የሚሉት ተጨማሪ ነገር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s