አንጨብጫቢ ትውልድ…

ረቡእ ማታ ከስራ ወጥቼ ቤት ለመድረስ እየተጣደፍኩ ነው፣ 6ኪሎ አከባቢ ስደርስ የተቀመጠበትን ዊልቼር እያሽከረከረ በፍጠነት ከፊት ለፊቴ መጥቶ ተደቀነ … ማሞ ተሰማ። ማሞ ባለዊልቸሩ።

እኔ – ኦ… ማሞ ነብሴ

ማሞ – ሰላም ነው በላይዬ (አቆላመጦ ነው እሚጠራኝ)

ተጨባበጥን፣ ድንቡሽቡሽ ጉንጩን ሳምኩት

ማሞ – ተጠፋፋን አይደል በላይዬ? ደሞ አመሮብሀል። ዋው! (ማድነቅ ይወዳል)

እኔ – አዎ ምንም አልል .. አልሐመዱሊላህ። የት እየሄድክ ነዉ?

ማሞ – እዚህ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የትያትር ፌስቲቫል ስላለ ትያትር ለማየት እየሄድኩ ነው፥ አብረን ብንሄድ ደስ ይለኛል።

እኔ – አረ ጣጣ የለውም እንሂድ አልኩ (ትንሽ ካቅማማሁ በሗላ)

ከሗላ ሁኜ ዊልቼሩን እየገፋሁለት ወደ ዩኒቨርስቲው ፣ ባህል ማእከል ገባን።

ትያትሩ ተጀምሮ ደረስን። ትያትሩ “ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ” ይሰኛል።

ሰዉ እስከ አፍ ጢሙ ስለሞላ ቆመን ለማየት ተገደድን። ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል

አንኩሮ ለመከታተል ብንችልም በዛው ለመቀጠል ግን አልታደልንም። ምክኒያቱ ወዲህ ነው…

– ተዋናዩ የአፄ ቴዎድሮስን ጀብድ ሲያስተጋባ … ከፊል ተመለካቹ በጭብጨባ አዳራሹን ያናዉጠዋል..

– ሀገርን የሚያወድስ፣ እንግሊዝን የሚያንኳስስ ፣ እምቢ ባይነት እና ወዘተርፈ ሲሰማ… እንደተለመደው… በጭብጨባ … ሲላቸው ደሞ በፉⶽት ይቀውጡታል።

ታድያ በእያንዷንዷ ጭብጨባ እና ፉⶽት ውሰጥ የማትደገም ቁም ነገር ታልፈናለች። ምን እንደተባለ ሳንሰማው ምስል ብቻ ተመለከትን።

በመጨረሻም አያልቅ የለም አለቀ። ወጣን።

እየወጣን ሳለ …ከፊሉ የተዋንያኖችን የትወና አቅም ሲያደንቁ፣ ከፊሉ የትያትሩን ይዘት ሲያወድሱ ..ግራ ቀኙን እየሰማን ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ወጣን።

ከዋናው በር አከባቢ ካሉት ሊስትሮዎች ቦታ ቆመን ስለ ተመልካቹ ስነምግባር ትንሽ አልንና ተለያየን።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s