የስቅላት ቅጣት ተፈፃሚነት በኢትዮጵያ

 

በላይ አዱኛ
ህዳር 13/2007

በኢትዮጵያ ኢህዴግ የስልጣን መንበሩን ከያዘበት እለት አንሰቶ እስከዛሬ ስቅላት የተበየነባቸው ወንጀለኞች የትዬለሌ ናቸው። ዳሩ ግን ብይኑ የፀናባቸው ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው። ሌሎቹ ደሞ ወደ እድሜ ልክ እስራት ዝቅ ብሎላቸው ያለ ቀረፅ ተኝተው ይመገባሉ። ለአብነት የደርጉ ሻለቃ ተፈራ መላኩን መጥቀስ ይቻላል። እንደሚታወቀው ሻለቃ መላኩ ጎንደር በነበረበት ወቅት ከ 16 ሺ በለይ ህዝብ የጨፈጨፈ አረመኔ ነበር። ለዚህም የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሲሰራ የተገኘ የሰዎች አፅም ብዛት አንዱ ማሳያ ነው። ሌላውን ሆድ ይፍጀው።

እነዛ ሁለቱ የሞት ብይን የፀናባቸው ወንጀለኞችን ስናይ ደሞ ባለስለጣናትን የገደሉ ናቸው። ባለስልጣናቱም ጄነራሎች ነበሩ ። እነሱም ሓየሎም አርአያ እና ክንፈ ገ/መድህን ናቸው።

ሜጀር ጄነራል ሓየሎም አርአያ በኢትዮጵያ መከፋፈል አልደራደር ሲላቸው አሰገደሉት፤ አንድ ኤርትራዊ

ገደለው ተባለ ምስኪን ገዳይ ተብየውም ወድያውን የሞት ፅዋውን እንዲⶸልጥ ተደረገ።
ጄነራል ክንፈ ገ/መድህን ደሞ መለስ ዜናዊ ላይ የሞት ሴራ መጠንሰሱን ሲሰማ ሚስጥር በማውጣት መለስን ከሞት ታደገ፤ ሚስጥር ማውጣቱን የደረሱበት ሴረኞቹ በሻለቃ ፀጋዬ አመካኝነት እንዲወገድ ተደረገ። ገዳዩ ሻለቃም በሰፈረበት ቁና መሰፈር አይቀርም እና በተራው ፅዋውን ጨለጠ።

ይህንን እንዲያው ለመንደርደሪያነት አልኩ እንጅ ጉዳዬ ወዲህ ነው። ባሳለፍነው አመት በአንድ የግል ትምህርት ቤት የ11 አመት ብላቴና በሶስት ወንድ አስተማሪዎቹ እረፍት ሰዓት እየጠበቁ መማሪያ ክፍል እየወሰዱ ይፈራረቁበት እንደነበርና ደፋሪዎቹ መምህራኑም ስድስት ስድስት አመት አንደተፈረደባቸው የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው። ታድያ ይህ ቅጣት መሰል ምቾት ብይን መቀጣጫ ሊሆን ይችላል ወይ? ሌሎች በዚህ አይነት ብልሹ ተግባር ውስጥ ለተሰማሩ ግለሰቦችስ ምን ትምህርት ይሰጣል? እንዲያውም የሚያበረታታቸው ይመስለኛል። እስቲ አስቡት ስድስት አመት ለስሙ ተፈረደባቸው እንጅ የአመኩሮ ግዜ ከታየላቸው በ3 ወይ ደሞ በ4 አመት ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ። ከማረሚያ ቤት ከወጡ በሗላስ ይህንን ተግባራቸውን አለመቀጠላቸውስ ምንድር ነው ዋስትናው? የጥቃት ሰለባዎቹስ ወደ ነበሩበት ሂወት የመመለስ እጣፈንታቸውስ እስከ ምን ድረስ ነው? እንደዚህ አይነት ከጥፋቱ አንፃር የማይመጣጠን ፍርድስ የሰለባዎቹን ቤተሰቦች ለበቀል አይጋብዝም ወይ?

ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴትትላላቹህ እውን የክርስቲያን ደሴት ከሆነች በመፅሀፍ ቅዱስ እምታምኑ ከሆነ እግዚአብሄር ግብረ ሰዶማውያንን በምን ነበረ ያጠፋቸው?

የሰዶም እና የጎሞራ ከተሞች በምን ነበር የተቀጡት? ላንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ በእሳት አልነበረም እንዴ የቀጣቸው?

ታድያ ይህ ከሆነ እነዚህ አረመኔ የሰው አውሬ በህፃናት ነብስ የሚጫወቱትስ ለሌሎች መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ለምን ላንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ በአደባባይ ሰቅለን ከዚች ዓለም አናሰናብታቸውም?

ምናልባት ይህ የፍርድ ቤት ስራ ነው፤ በዳኝነት ስራ እጃችንን አናስገባምትሉን ይሆናል። ዳኛውስ ቢሆን ከየት አምጥቶ ነው አሚፈርደው? እራሳቹህ በከተባችሁት የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት አይደለምን? የወንጀለኛ መቅጫ ህጉስ ለምን አይሻሻልም? ከሰማይ የወረደ ነውን? ስለምንስ ታዛቢ ትሆናላቹህ፣ እንሆናለን?

ሴቶች ድሮ ማጀት ውስጥ ነበሩ እድሜ ለልማታዊው መንግስታችን አደባባይ እየወጡ ነው፤ ት/ት ቤቶች አየተሰሩ ነው ፤ ይሄን ያህል ሴቶች የመማር እድል አግኝተዋልትላላቹህ።

ማለታችሁ ባልከፋ ነገር ግን ከቤትወደ ት/ት ቤት ፣ ከት/ት ቤት ወደ ቤት እሚመላለሱበትን ጎዳና ከደፋሪ እና ጠላፊ የሰው አውሬ ምን ያህል ፅዱ ነው? የሚለውን ጥያቄ መጀመሪያ መልሳችሗል? እንዳልመለሳችሁት እርግጠኛ ነኝ። ምክኒያቱም ይሄው በመዲናችን አዲስ አበባ እንኳ ቀንበጧ ሀና ላላንጎ ከት/ት ቤት ወደ ቤቷ በሰላም መመለስ አልቻለችም። ለ5 ሲፈራረቁባት ሰንብተው ሜዳ ላይ ጣሏት። ሞተች። አሁንስ ጥያቄውን መልሰናል ትላላቹህ?

የሀና ጉዳይ መቸም ትንሽ የነቃ ህብረተሰብ ባለባት እና የሚድያዎች ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ሆነ እንጅ ገጠር ውስጥ ያለውን ቤት ይቁጠረው ፤ ብርቅ እይደለም። የእያንዳነዳችንን በር እያንኳኳ ያለ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ስንቶቻቸው ናቸው የፊስቱላ ሰለባ የሆኑ እህቶቻችን እና እናቶቻችን በየሆስፒታሉ እሚያጣጥሩት?? ቀንበጧ ሀናስ አንዴ ተገላግላዋለች። ቀሪዎቹ እናቶቻችን እና እህቶቻችን ምንድር ነው ዋስትናቸው?

ለግላጋዋን ቀንበጥ ሀና ላላንጎን በእንጩጩ የቀጠፏት የሰው አውሬዎች በሰፈሩበት ቁና እንደሚሰፈሩ ተሰፋ አደርጋለሁ።

የሂወት ዋስትና ለእህቶቻችንና ለእናቶቻችን —- ፍትህ ለቀንበጧ ሀና !!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s