የዛሬ የሐና ጉዳይ የፍርድ ቤት ውሎ እንዲህ ይመስል ነበር

በአዜብ ወርቁ ተፃፈ
ስለዛሬው ቀጠሮ ጉዳይ ለመነጋገር ለሐና ቤተሰቦች ትላንት ማታ ስንደውል ባለፈው ከጠዋቱ በ12 ሰዓት በዝግ ችሎት መታየቱን በማስታወስ ነገ ከሌሊቱ 12 ሰዓት ለመሄድ ወስነናል አሉን እና ተቀጣጠርን እኛ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ስንደርስ እነሱ ከሌሊት 11 ሰዓት ደርሰው ሲጠባበቁ አገኘናቸው፡፡ 11 ሰዓት ላይ የፍርድቤቱን በር ሲያንኳኩ ጥበቃው መቼ ነጋ? ፍርድቤት በሌሊት መስራት ጀመረ እንዴ ብሎ ተደናገጠ አሉ፡፡ እኛም ባለፈው ይሄን ጥያቄ ጠይቀን ነበር ግን በሌሊት በ12 ሰዓት ማየት ጀምረናል ሲሉ እንግዲህ ቢጀምሩ ነው ብለን አምነናቸው ነው ፡፡ በሌሊት መጥተን ፍርድ ቤቱ እስኪከፈት እስከ 3 ሰዓት ድረስ በር ላይ ቆመን ስንጠባበቅ ቆየንና በሩ ወለል ብሎ ለባለጉዳዮች ሲከፈት ገባን እስከ 4 ሰዓት ድረስ ተጠባበቅን መረጃ ጠያየቅን እዚህ ሳይሆን ልደታ ፍርድቤት ተዘዋውሯል እዚህ አይቀርብም የሚል ነገር ሰማንና ሁለት ሆነን ሌሎቹን እዛ ትተን ልደታ ለማጣራት ሄድን ልደታ እነሱ ጋ እንዳልደረሰ እና ሜክሲኮ የሚገኘው አንደኛ ፍርድቤት እንደሆነ ተነገረን ተመለስን ሜክሲኮ ፍርድቤት ደግሞ በተያዘለት ቀጠሮ መሰረት በዕለቱ እዛው እንደሚቀርቡ ግን ወደ ረፈዱ ላይ እንደሚሆን ተነገረ ተባለ እና ተበታተንን ፡፡

በመጨረሻም 10 ሰዓት ላይ ቀረቡ እና ምርመራው ስለተጠናቀቀ ወደ ከፍተኛ ፍርድቤት እንደተላለፈ እና ዕሮብ ታህሳስ 8 ከፍተኛው ፍርድቤት እንደሚቀርቡ ሰማን
ደስ ይላል የምርመራ መዝገቡ ተጠናቆ ወደ ከፍተኛ ፍርድቤት መተላለፉ ትልቅ ነገር ነው፡፡
ነገር ግን አንድ መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ አለ
ለምንድነው ተጠርጣሪዎቹ ፍርድቤት የሚቀርቡበት ሰዓት እና ጉዳዩ ሚስጢር እንዲሆን የተፈለገው?
ግርግር እንዳይፈጠር ጸጥታ እንዳይደፈርስ ነው የሚባል ነገር ሰምቻለሁ በማን ?
እንዴ ፍርድ ቤት ተገኝታችሁ እኮ ብትመለከቱ ባለፈው ከቅርብ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶች ውጪ ከለቤተሰቦቿ አይዞአችሁ አብረናችሁ ነን ለማለት እና በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር ማዘናችንን ለማሳየት የተገኘነው ሰዎች 10 ብንሆን ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ጠዋት ከቤተሰቦቿ ውጪ የነበርነው 3 ነበርን ለዘውም ተከፋፍለን አንዳችን ጠዋት ሁለቱ ከሰዓት እንዴት ነው ግርግር እና ጭንቅንቅ የታየው?
ለምንድነው የሐና ቤተሰቦች በልጃቸው መጎዳታቸው ሳያንሳቸው እንደገና ፍትሕ ፍለጋ የሚጉላሉት?
ከሰዓት 10 ሰዓት ላይ ለሚቀርብ የምርመራ መዝገብ እነሱ ከ ሌሊቱ 11 ሰዓት የፍርድቤት በር ማንኳኳት እና በዛ ውርጭ በሩን የሙጥኝ ብለው መጠበቅ ትክክለኛውን ጉዳዩ የት እንደሚታይ የሚናገር መረጃ የሚሰጥ ጠፍቶ አንዱ ፒያሳ አንዱ ልደታ አንዱ ሜክሲኮ መንከራተት ለምን አስፈለገ?
እረ ለተጎጂ ቤተሰቦች አክብሮት እና እንክብካቤ በመስጠት ከልብ መቆርቆራችንን እና ሐዘኔታችንን እናሳይ
ፍትሕ ለሐና!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s