“ካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች ለአምልኮ የሚጠቀሙባት በተለምዶ ድንግል ማርያም እና ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እየተባለ የሚመለከው ስእል እናት እና ልጅ ማን እንደሆኑ ያውቃሉ? እንግዲያውስ ዛሬ ይወቁትና እርሞትን ያውጡ! ድንግል ማርያምን መስላ የምትመለከው “ሰመራሚስ” ስትባል ኢየሱስን መስሎ የሚመለከው ደግሞ የሰመራሚስ ልጅ “ናምሩድ” ነው:: ናምሩድ ሚስቱ ሰመራሚስ ትክክለኛ እናቱም ሚስቱም ነች::”

Untitled-2

“እምነት” እንደ “ቁስ” (እቃ) አይደለም! “እምነት” ከቅድመ አያት : ከአያት : ከአባትና ከእናት አይወረስም! “እምነት” በማስረጃ ተረጋግጦ በሚገባ ተረድተነው የምንቀበለው የነጻነት እውነተኛ መንገድ ነው:: ይህ እውነተኛ የክርስትና እምነት መሰረቱ የትኛውም ሐይማኖት : ግለሰብ : ህብረተሰብ : ባህል : አገር ወይምታሪክ አይደለም! መሰረቱ የእግዚያብሔር ቃል የሆነው “መጽሐፍ ቅዱስ” ብቻ ነው!!!”          

“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል::” ዮሐ8:32

ክፍል አራት

ቢንያም መንገሻ December 16,2014

የእግዚያብሔር “ሴቶች” ልጆችን ዲያብሎስ (ሰይጣን) ለመንግስቱ የጥፋት ስራ ማስፈጸሚያ እንዲያገለግሉት ከመቼ ጀመረ? ከየትኛዋ ሴት ጀመረ? በየትኛዋና በመጨረሻዋ ሴት ላይ የመጨረሻው የእርኩሰት ጥፋቱን ይጨረሳል?

ዲያብሎስ የእግዚያብሔር ሴት ልጆችን ለጥፋቱ ማስፈጸሚያ ስራ ከመረጣቸውና ማሰራት ካስጀመራቸው እነሆ ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ እንዲሁም እስከ እዚህች አለም ፍጻሜ ድረስ ሴቶች ለዲያብሎስ መንግስት የእርኩሰት ስራ ማስፈጸሚያ የጥፋት አምልኮ ስራ ዋናውን ድርሻ ይይዛሉ:: ሁላችንም የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቀው አንድ ታሪክ አለ እርሱም የመጀመሪያዋ የሰው ልጅ ዘር እናት የምትባለው ሄዋን ለመጀመሪያ ግዜ በዲያብሎስ አሳሳች ስብከት ተታላ ፈጣሪዋና አምላክዋ እግዚያብሔር ያዘዛቸውን ትእዛዝ በመተላለፍዋና ለባሏም ለአዳም እንዲሳሳት ዋና ምክንያት በመሆኗ ምክንያት እነሆ ለመጀመሪያ ግዜ ዲያብሎስ በሴቱ ዘር ልብ ውስጥ ገባ:: የሰው ልጅ ዘር መጀመሪያ እናት የሆነችው ሄዋን ለመጀመሪያ ግዜ ለዲያብሎስ የሀሰተኛው መንግስት የእርኩሰት የሀጢያት መስፈጸሚያ “ሴት” ሆና ተመረጠች::

adamandeve

ሴቶችን ለመንግስቱ ጥፋት የመረጠው ዲያብሎስ በሄዋን የጀመረውን የማስካድ ስራ በሁለተኛዋ ሄዋን በ “ማርያም” ስም ለማሳሳቻ ተጠቅሞ በመጨረሻዋ የዘመን ፍጻሜ የምትገለጠውን የ“ታላቂቱ ጋለሞታ”ን የመጨረሻ የራዕዩ መገለጫ ሴት አድርጎ በመጠቀም የዚህን አለም የመጨረሻ የራሱ እና ሌሎችም የእግዚያብሔር ፍጡር የሆኑ ሰዎችን በማሳሳትና ከእውነተኛው ከእግዚያብሔር ቃል በመለየት ለዘላለም የጋህነም እሳት ፍርድ የማገዶ እንጨት አድርጎዋቸዋል ::

ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደምንረዳው ዲያብሎስ ( ሰይጣን ) በሄዋን የጀመረው ሴቶችን የመጠቀም ሚስጥር በተለያዩ ግዜና በተለያዩ የእግዚያብሔር ሰዎች በሚስቶቻቸው እንኳ ሳይቀር ዲያብሎስ መሰሪ የሆነ በሴት የመጠቀም ጥበቡን አሳይቷል::

ለምሳሌ ለአብነት ያህል ብንጠቅስ አብርሀም እግዚያብሔር የሰጠውን ተስፋ በመጠራጠር የሚስቱ የሳራን ምክር ሰምቶ ወደ ገረዱ አጋር በመግባቱና ልጅ በመውለዱ የዚህ አለም ሀይማኖታዊና ፓለቲካዊ ታላቅ ችግሮች ተፈጠሩ:: ማለት ሁለት መንግስቶች ተፈጠሩ ከአንድ አባት ከሁለት ሴቶች ሁለት ታላላቅ ህዝቦች በዚህ አለም ተፈጠሩ:: አንዷ ሴት በመከረችው ምክር አለም ተናጋ አንዷ ለመዳን ከእግዚያብሔር የተስፋ ልጅ ስትወልድ አንዷ ለጥፋት ከሰው ሀሳብ ልጅ ወለደች:: አንዷ የእግዚያብሔርን መንግስት ስትወክል አንዷ ደግሞ የዲያብሎስን መንግስት ወክላለች:: ሌላው በሴት የወደቁት ታላላቅ የእግዚያብሔርን ሰዎች ብንመለከት ለምሳሌ ሳምሶን : ንጉስ ዳዊት : ጠቢቡ ሰለሞን ሌሎችንም ልናነሳ እንችላለን ዲያብሎስ ትልቁንና ዋናውን የጥፋት ስራ የሚሰሩለት ሴቶች ናቸው:: እዚህ ላይ ሁሉም ሴቶች አይደሉም ለእግዚያብሔር መንግስትም በጽድቅ ስማቸው በቅዱስ መጽሐፍት የተጠራ ሴቶችም እንዳሉ መዘንጋት የለበትም::

“እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም። በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ሴቲቱም ለእባቡ አለችው። በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን፤ ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ። እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም። እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ። እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም። እግዚአብሔርም አለው። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን። ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች። እባብ አሳተኝና በላሁ። እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው። ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ። በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። ለሴቲቱም አለ። በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል። አዳምንም አለው። የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና። አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።” ዘፍ 3

“አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤ ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች።” 1 ጢሞ2:13_15

ዲያብሎስ (ሰይጣን) እራሱን በሴቶች በኩል በመግለጥና በማሳሳት እንዲሁም በሐይማኖት ስም እንዲመለኩ ለመጀመሪያ ግዜ ከማን ጀመረ? የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ተመላኪ ሴት አማልክት ማን ናት? በማንና በምን ተመስላ ትመለካለች?

8

“ ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው፤ ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞላች። ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፥ ወይንም ተከለ።ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ዕራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ።እንዲህም አለ። ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ። የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።” ዘፍ 9:18_27 “የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው። ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።” ዘፍ 10:1_10

curse-of-ham

ከላይ በዘፍጥረት ከላይ በተጠቀሱት ምእራፎች የተጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ታሪኮች በጥንቃቄ ስናነብ ከታላቁ የጥፋት ውሀ ከተረፉት የኖህ ቤተሰቦች ውስጥ ታላቁ የእግዚያብሔር ሰው ኖህ አንዱን ልጁን እንዲህ በማለት ሲረግመው እናነባለን “ ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ።እንዲህም አለ። ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ። የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር፤ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።”

cush-putking_nimrod02

እግዚያብሔር ስለ ናምሩድ እንዲህ ነበር ያለው “ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።” የመጽሐፍ ቅዱስና የጥንታዊ ስነ ቅርስ አጥኝዎች እንደሚያስረዱት ናምሩድ እጅግ ግዙፍ ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን በተጨማሪ ከሰው ተፈጥሮ ማንነት በላይ የሆነ እጅግ የተለየ ማንነት ያለው ናምሩድ የኔፍሌምስ (የወደቁት መላእክት) ወይም የዲያብሎስ ዘር ነው ይሉናል ጥናቱን ያጠኑት የመጽሀፍ ቅዱስ አጥኚዎች :: በቅጽል ስሙ የጥፋት ሰው የሚባለው ናምሩድ የታላቋን ባቢሎንን ከተማ የገነባ ታላቅ የዓለማችን ጥቁር ንጉስ ነው:: በተጨማሪም የአለም መንግስታቶች አሁን የሚጠቀሙበትን ህግ ያረቀቀ ታላቅ የጥፋት ሰው ነው ናምሩድ:: በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚያብሔር ስለ ናምሩድ ታላቅ አዳኝነቱ ሲነግረን የሚያድነው የጫካ እንሰሳ ሳይሆን ህዝቦችንና አገሮችን ሲሆን እንደ መጽሀፍ ቅዱስ አጥኝዎች አገላለጽ ናምሩድ ታላቅ የምድራችን ሀይለኛ ጦረኛ ሰው ጭምርም ነው :: ናምሩድ የጥፋት ሰው ከጥፋት ውሀ ቡኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በምድር ላይ እግዚያብሔር መንፈሱ የሚጸየፋቸውን የጥንቆላ : የአስማት : የመተት ድግምት ስራዎች እንዲሁም የጣኦት (የሰይጣን) አምልኮ ያስጀመረ ታላቅ የጥፋት ሰው ነበረ::

semiramis n nimrodvirgin-mary-wallpapers-1310fatima17

ናምሩድ ሌላው የሚመሰለው የጸሐይ አምላክ ሲሆን ሚስቱ ደግሞ ሰመራሚስ “የሰማይ ንግስት” (Queen of Heaven) : “የእግዚያብሔር እናት” (Mother of God) እንዲሁም የጨረቃ አምላክ ነች:: ሰመራሚስ ለናምሩድ እናቱም ሚስቱም ነች::

nimrodGiovanni_Francesco_Barbieri,_Semiramis_Receiving_Word_of_the_Revolt_of_Babylon_(1624)Imagenes-religiosas-de-la-virgen-maria-2

ሰመራሚስ ለናምሩድ እውነተኛ እናቱ ስትሆን ናምሩድ አባቱን ገድሎ ነው እናቱን ያገባው:: ሰመራሚስ አይ . ኤስ . አይ . ኤስ (ISIS) ስትሆን የሁሮስ አይን የሚባለው ደግሞ የናምሩድ አይን ነው:: ናምሩድ የተወለደው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ዲሴምበር 25 ላይ ነው:: የሁሮስ አይን የሚባለው የሚስጥራዊው ማህበር “ኢሉሚናቲ 666” ( Illuminati 666) የሚጠቀሙበት የግብጽ ፒራሚድ ላይ ከአንድ አይን ጋር ያለው አርማ ናምሩድን ሲወክል ሰመራሚስ አይ . ኤስ . አይ . ኤስ (ISIS) (ISIS) ደግሞ የካቶሊክና ኦርቶዶክስ ለአምልኮ የሚጠቀሙባት የማርያምን ምስል ትወክላለች:: በተጨማሪ የካቶሊኳ እና የኦርቶዶክሷ ማርያም እውነተኛዋ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማርያም አይደለችም::

illuminati3ISIS HORUS MARY JESUS

የካቶሊኳና የኦርቶዶክሷ ማርያም ህጻን ልጅ ታቅፋ የምትታየው ማርያም ሀሰተኛዋ ማርያም “ሰመራሚስ” ስትሆን በእጇ የያዘችው ህጻን ሀሰተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ “ናምሩድ” ነው::

The Passion of the Christ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዮሐንስ ወንጌል በተሰራው ፊልም ላይ ጌታ ኢየሱስ ሲገረፍ : ሲሰቀልና ሊሞት ሲል ዲያብሎስን መስላ በስውር ስትከታተለው የነበረች ሴት በስተመጨረሻ ጌታችን ሲሰቀል አንድ ህጻን ልጅ ይዛ የምትታየዋ ሰመራሚስ እና ልጇ ናምሩድ ሲሆን The Passion of the Christ ፊልም ይህንን ጽሁፍ በደንብ ያጠናክረዋል::

004POC_Rosalinda_Celentano_003MARY-2

የናምሩድ ሚስት “ሳመራሚስ” የስሟም ትርጉም የሀጢያት ስጦታ ማለት ሲሆን ሳመራሚስ ከሚገባው በላይ በጣም ውብ ሴት ናት በተጨማሪም ይህች ውብ የናምሩድ ሚስት የፀሐይ እና የጨረቃ የሰማይ ንግስት በመባል የምትታወቅ ሲሆን የ በባእድ አምልኮ አማልክትነቷ የምትታወቀው ሰሜራሚስ በተጨማሪም የልዬ ልዩ የሳይንሳዊ ጥበብ : የስነ ህንጻ ጥበብ : የስነ ክዋክብት ቆጠራ ጥበብ : የጥንቆላ : የአስማት : የመተት : የድግምትና የዝሙት አምልኮ ፈጣሪ ስትሆን በተጨማሪ የሴት ጣኦት (አማልክት) አምላክ ጭምር ናት::

images ssemiramis f

ታላቁ የአመጽ ሰው ናምሩድ ለእዚች ሚስቱ የባቢሎንን ከተማ መስርቶላታል በመጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን አሁን ላይ የምትገለጠው የክፋቷ እናት ታላቂቷ ጋለሞታ የባቢሎን እርኩስ መንፈስ የናምሩድ ሚስት “ሰመራሚስ” ስትሆን ሰመራሚስ የተለያዬ የአምልኮ መጠሪያ ስሞች አሉዋት ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ “የሰማይ ንግስት” : ዲያና : አስታሮት : እንዲሁም የእግዚያብሔርን ነብያቶች የምታስጨንቀው ኤልዛቤል የዝሙት መንፈስ የሰመራሚስ መንፈስ ነው:: በተጨማሪ ሰመራሚስ በመጨረሻው ዘመን የምትገለጠው በራእይ መጽሐፍ ላይ ያለችው ጋለሞታይቱ ሴት ጭምር ናት::

tower_of_babel.170113154rev17

ጠቢቡ ሰለሞን እንኳ በመጨረሻው የንግስና ዘመኑ ሰመራሚስ “የሰማይ ንግስት” (Queen of Heaven) : “የእግዚያብሔር እናት” (Mother of God) አምልኳት የነበረ ሲሆን እግዚያብሔርም ታላቁን ቁጣውን እንደሚቀጣው ገልጾለትም ጭምር የነበረ ሲሆን መንግስቱንም ለሌላ መንግስት ሰጥቶበታል::  “ንጉሡም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፥ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያን በሲዶናውያንና በኬጢያውያን ሴቶች፥ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ። እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች። አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ። ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት። ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ። ለአማልክቶቻቸው ዕጣን ለሚያጥኑ መሥዋዕትም ለሚሠዉ ለእንግዶች ሚስቶቹ ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳይከተል ካዘዘው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡን አርቆአልና፥ እግዚአብሔርም ያዘዘውን ነገር አልጠበቀምና እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቈጣ። እግዚአብሔርም ሰሎሞንን አለው። ይህን ሠርተሃልና፥ ያዘዝሁህንም ቃል ኪዳኔንና ሥርዓቴን አልጠበቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ቀዳድጄ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ። ነገር ግን ከልጅህ እጅ እቀድደዋለሁ እንጂ ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘመንህ አላደርግም።” 1ነገ 11:4_6

640px-AiKhanoumPlateSharp

እስራኤሎች ብዙውን ግዜ ሰሜራሚስ “የሰማይ ንግስት” (Queen of Heaven) : “የእግዚያብሔር እናት” (Mother of God) የሚያመልኳት ሲሆን እግዚያብሔርም በእዚህ አጸያፊ ስራቸው ብዙ ግዜ ይቆጣቸውና ያዝንባቸው ነበር:: “ሚስቶቻቸውም ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፥ በግብጽ ምድር በጳትሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ መለሱለት እንዲህም አሉ። አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም። ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፥ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቁርባን እናፈስስላት ዘንድ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር። ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርስዋም የመጠጥን ቍርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፥ እኛ በሁሉ ነገር ተቸግረናል፥ በሰይፍና በራብ አልቀናል። እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?” ኤር44:45_49

“ናምሩድ እና ሰመራሚስ” በአለም ባሉ ህዝቦች ዘንድ ዛሬ ላይ ብዙ የተለያዩ መጠሪያ ስሞች አሉዋቸው ከሚጠሩበት ብዙ ስሞች ጥቂቶቹን እንደሚከተሉት ይነበባሉ:

lImagenes-religiosas-de-la-virgen-maria-5

አላህ ወይም አለላህ (Allilah or Allah ) :

MeccaMosque1010eJordan's King Abdullah performs the Umrah in Mecca

“የሰማይ ንግስት” (Queen of Heaven) : “የእግዚያብሔር እናት” (Mother of God) : “ የጨረቃ አምላክ ” (Moon God) :

640px-Fra_Bartolomeo_004307377_528523180512364_1685922407_n - Copy

“የጸሐይ አምላክ” : “ድንግል ማርያም” : “ፋጢማ” : “ጥቁሯ ማርያም” (Black Madonna) : “ሁሮስ” (አይ . ኤስ . ኤስ . አይ . ISIS) የግብጻውያን የጸሀይ አምላክ :

5078C20maddona1Imagenes-religiosas-de-la-virgen-maria-1

“አርዴን” : “አስተራት” : “ሳይቤለእ 12 ኮከብ በጭንቅላቷ ላይ የያዘች ሴት አምላክ” : “ዲያና” : “ኢሽታር” ባቢሎናውያን የጸሐይ አምላክ : “ላክስጂሚይ” : “የነጻነት ሴት” (Liberty) : “ሪይሐ” አጥማጁ አምላክ : “ሲን” የጨረቃ አምላክ : “ቪነስ” የፍቅር አምላክ ሲሆኑ በኢስላም : በካቶሊክና በኦርቶዶክስ የእምነት ቤት ውስጥ በሀይማኖት እና በድንግል ማርያም ስም “ ናምሩድ እና ሰመራሚስ” በግልጽ ይመለካሉ::

monstrance pope-benedictla-apphoto-aptopix-obama-us-vatican-jpg-20140327

“ናምሩድ እና ሰመራሚስ” ዛሬ መንፈሳቸው ያለንበትን አለም በብርቱ ጠፍንጎ ይዞታል:: ዛሬ የአለም መንግስታቶች የ“ናምሩድ እና ሰመራሚስ” እርኩስ መንፈስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናቸው:: ዛሬ ላይ የአብዛኛው የአለም አገር ታላላቅ የመንግስት ተቋማት : በአለም ላይ ያሉ አገሮች መለያቸው የሆነው ሰንደቃቸው (ባንድራ) : ታላላቅ የግል ተቋማት : የመዝናኛው ኢንዱስትሪ : ታላላቅ የሚባሉ የሀይማኖት ተቋማት የክርስትያኖችን ጨምሮ የ“ናምሩድ እና ሰመራሚስ”ን ምስልና የሚወክላቸውን ቅርጽ ያለበትን አርማ ይጠቀማሉ::

1348632198141348520110447604_444892215650428_5116822382174902084_nbeyonce-illuminati-montage

የ“ናምሩድ እና ሰመራሚስ”ን በግልጽ ያመልካሉ:: አገራችንም ኢትዮጵያም በተለያየ ግዜ የነገሱ ነገስታቶችና መንግስቶች በተጨማሪ በሀገሪቱ የመጀመሪያውና ትልቁ የሀይማኖት ተቋም የሆነው ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ጨምሮ “ናምሩድ እና ሰመራሚስ”ን የሚወክሉትን አርማዎች በሰንደቅ (ባንድራ) ላይና በመንግስት ቢሮ አርማዎች እንዲሁም በጥንት ውቅር አብያተ ቤተክርስትያን ህንጻዎች ላይ የተቀረጹ ቅርጻ ቅርጾችና ስእላ ስእሎች ላይ ሲጠቀሙበትና ሲያመልኩት በግልጽ ለማየት ይቻላል::

bushiran19353-logo

ከዚህ ቀደም ስለ ሚስጥራዊው ማህበር “ኢሉሚናቲ 666” (Illuminati 666) በጻፍኩት ጽሁፍ ላይ ስለ በአለማችን ላይ “ኢሉሚናቲ 666” አርማ የሚወክለው “ናምሩድ እና ሰመራሚስ” ሲሆን ይህንን አርማ የሚጠቀሙ አለም አቀፍ መንግስቶችና ድርጅቶች እንዲሁም ታዋቂ የአለማችን ሰዎች የሚጠቀሙበትን አርማ ለማወቅ ከፈለጉ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ::

https://binjaminia.wordpress.com/2014/06/21/r/

ሁሌም ክርስትያንና በሌሎቹም አይነት ሐይማኖቶች ተመስለው ጣኦት የሚያመልኩና የሚያስመልኩ የሐይማኖት ቤተእምነት ሰዎች የጣኦቶቻቸው ገበና ሲጋለጥባቸው ጸያፍ በሆነ ቃል ይሳደባሉ : በመጥፎ ይከሳሉ : ያጋለጠውን ሰውንና ቤተሰቡን ካገኙ ይደበድባሉ : ያሳስራሉ: ይገድላሉ ያስገድላሉ::

chrislam0fatima_portugal_11

“ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚሉት አንድ ሰው የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች በብር እየሠራ ለአንጥረኞች እጅግ ትርፍ ያገኝ ነበርና፤ እነዚህንም ይህንም የሚመስለውን ሥራ የሠሩትን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው። ሰዎች ሆይ፥ ትርፋችን በዚህ ሥራ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ። ይህም ጳውሎስ። በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል ሰምታችሁማል። ሥራችንም እንዲናቅ ብቻ አይደለም፥ እስያ ሁሉ ዓለሙም የሚያመልካት የታላቂቱ አምላክ የአርጤምስ መቅደስ ምናምን ሆኖ እንዲቆጠር እንጂ፥ ታላቅነትዋም ደግሞ እንዳይሻር ያስፈራል። ይህንም በሰሙ ጊዜ ቍጣ ሞላባቸው። የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉም ጮኹ። ከተማውም በሙሉው ተደባለቀ፥ የመቄዶንያም ሰዎች የጳውሎስን ጓደኞች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ከእነርሱ ጋር ነጥቀው በአንድ ልብ ሆነው ወደ ጨዋታ ስፍራ ሮጡ። ጳውሎስም ወደ ሕዝቡ ይገባ ዘንድ በፈቀደ ጊዜ ደቀ መዛሙርት ከለከሉት። ከእስያም አለቆች ወዳጆቹ የሆኑት አንዳንዶች ደግሞ ወደ እርሱ ልከው ወደ ጨዋታ ስፍራ ራሱን እንዳይሰጥ ለመኑት። ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለ ምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና። አይሁድም ሲያቀርቡት፥ እስክንድሮስን ከሕዝቡ መካከል ወደ ፊት ገፉት፤ እስክንድሮስም በእጁ ጠቅሶ በሕዝብ ፊት እንዲምዋገትላቸው ወደደ። አይሁዳዊ ግን እንደ ሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ። የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ። የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?”ሐዋ 19

20130603nw863Mary worship

“ለሕዝቡም ሲናገሩ የካህናት አለቆችና የመቅደስ አዛዥ ሰዱቃውያንም፥ ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ ተቸግረው፥ ወደ እነርሱ ቀረቡ፥ እጃቸውንም ጭነውባቸው አሁን መሽቶ ነበርና እስከ ማግሥቱ ድረስ በወኅኒ አኖሩአቸው። ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ። በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ እነርሱንም በመካከል አቁመው። በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ? ብለው ጠየቁአቸው። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው። እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው። መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ። ከሸንጎም ወደ ውጭ ይወጡ ዘንድ አዝዘው። በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፥ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው። እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም አሉአቸው። እነርሱም እንደ ምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደ ገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።” ሐዋ ምዕራፍ 4

ይቀጥላል…….

ማራናታ!!!

“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል::” ዮሐ8:32

“የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።” ማቴ 24:37_40

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s