”ሞቼ ተነሳሁ” የሚለው ሰውዬ – “መለስ ዜናዊን ገነት አገኘኋቸው” አለ

የሀይማኖት ፣ የሞራል ወይስ የማንነት ግጭት ፍለጋ ?

ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

ሰሞኑን ራሱን ነብይ ብሎ የሚጠራ ዳንኤል አበራ የተባለ የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ሰው ለ5 ቀናት ሞቶ ሲኦልና ገነትን ጎብኝቶ እንደመጣ በመግለጽ የ5 ቀናት ቆይታውን (የጉዞ ማስታወሻውን እንበለው) ” እውነተኛው ዓለም ሲገለጥ” በሚል ርዕስ መጽሐፍ ጽፎ 279 ገፅ ያለውን መጽሐፍ በብር 350:00(ሦስት መቶ ሀምሳ) እየሸጠ ይገኛል። ሰማይ ቤት ደርሶ መመለስም ሆነ በነፃ ገበያ ሀገር 3,000:00 መሸጥም መብቱ ነው። ለማንኛውም መጽሐፉ በነፃ እጄ ገብቷል ። ካሁን ቀደም ” ማርያም ታየች ” ብሎ ህዝብ ሲያጋፋ የነበረ ባህታዊ ነኝ ያለ ሰው ፣ “ማርያም ነኝ” ብላ ክርስቶስ ነው ካለችው ትንሽ ልጅ ጋር ዞራ ስታጭበረብር የታሰረች ሴትን አውቃለሁ። እነዚህ ሰዎች የሚታለል ሲያገኙ አታለሉ እንጂ በዳንኤል ልክ የማንንም ሀይማኖት ፣ ሞራልና የየደጋፊያኑን ሰብእና የነኩ አልነበሩም ። ዳንኤል ግን ሀይማኖት ስም በመጽሐፉ የሚከተሉትን በዝምታ ሊታለፉ የማይገቡ ፣ ሀይማኖተኞችና ደጋፊዎቹ ህግ ፊት ሊያቆሙት የሚገባ ጥፋት ፈፅሟል።

daniel-abera

ለግል ኪሱ መዳጎስ በህትመት ስሌት 279 ገፅ መጽሐፍ ከ50 – 60 ብር ሊሸጥ ሲገባ 350 ብር የሚሸጠው ይህ ሰው ነውርን በውድ ዋጋ እየሸጠ ይገኛል ። ስለመጽሐፉ በተከታታይ የምለው ያለኝ ሲሆን ዋና ዋና ያልኳቸውን (ከመጽሐፉ የተገኙ) ጥቂት ሃሳቦችን ብቻ አነሳለሁ። ይህ ሀሳብ የሰውየው የግል ሀሳብ እንጂ የሀይማኖቱ እምነት አይደለም ብዬ ስለማምን ዋንኛውን ተቃውሞ ከጤነኞች የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታዮች እጠብቃለሁ። ለአንባቢያን ስሜት ሲባል ይህን ጽሑፍ በዝምታ ባልፈው በወደድኩ። ይሁን እንጂ ደግሞ ዝምታው ሀሳቡ ያለከልካይ እንዲራባ ከማድረግ ውጭ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። ከሞራል አንፃር ደግሞ ያለማለፍ ግዴታ ያለብኝ ሆኖ ተሰማኝ። በመሆኑም ለማስቆጣው የአንባቢያን ስሜት በቅድሚያ ይቅርታ አየጠየቅሁ ለዛሬው ይህን ልበል።

ከ”እውነተኛው ዓለም ሲገለጥ ” የተገኘ

★እየሩሳሌም ቅድስት ከተማ አይደለችም ።
★ነብዩ መሀመድን የእሳት ወንዝ ውስጥ ተጥሎ አየሁ።
★በህንፃው ውስጥ (በሲኦል ውስጥ ማለቱ ነው) መሀመድን የሚመስል መንፈስ ቁጭ ብሎ ‘አላህ ነኝ‘ በማለት ያደናግር ነበር።
★ አቡነ ጳውሎስን ጨምሮ የኦርቶዶክስና ካቶሊክ ጳጳሳት ከነአማኞቻቸው በእሳት ጉድጓድ እየተቃጠሉ በእሳት ጉድጓድ ተጥለው እየተቃጠሉ ሲሰቃዩ አይቻለሁ ።
★ጥላሁን ገሰሰ ከብዙ ግብረአበሮቹ ጋር በእሳት እየነደደ አየሁ ። ከዚያም “ምነው ከነሙሉ አካሌ በሞትኩ ፣ ለምን እግሬን አስቆረጥኩ” እያለ ማባሪያ በሌለው ፀፀት እርግማን ማውረዱን ተያያዘው ።
★የቀድሞው የሀገራችን መሪ (አቶ መለስ ዜናዊን ማለቱ ነው) በገነት እንዳገኛቸውና አየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያው ገነት የገባ መሪ መሆናቸውን እንደነገረው ከብዙ ሀተታዎች ጋር ጽፏል ።

Source: RevolutionForDemocracy

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s