“ፕሮተስታንቲዝምና ሊበራሊዝም”

አንድ Yonas Abera የተባለ ወንድማችን ስለ ፓስተር ተከስተ (ባለፈው ማገጠ ስለተባለው ፓስተር) በድሬ ቲዩብ ኮሜንት የሰጠውን ተንተርሼ ይሄንን ብያለሁ።
ማሳሰቢያ፦ ምላሽ ለመስጠት የተገደድኩት ፕሮቴስታንት ሁኜ ሳይሆን ያለአግባብ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ላይ ፅንፍ በያዘ አስተሳሰብ የስድብ ናዳ ስላወረደባቸው ነው። እኔ ምንም እንኳ ሙስሊም ብሆንም
ፕሮቴስታንት ወንድሞች፣ እህቶች፣ ጓደኞችና ጎረቤቶች አሉኝ።

ዮናስ አበራ ያለውን ላስቀድም

ፕሮተስታንቲዝምና ሊበራሊዝም

በፕሮተሰታንት አስተምህሮ የግል አዳኝ የሚለዉ አስተሳሰብ የእምነታቸዉ መሰረት ነዉ፡፡ በእርግጥ እሱም ቢሆን እምነት ካላቸዉ ነዉ፡፡ በመሰረቱ የግል አዳኝ የሚለዉ አስተሳሰብ ምንም ሀይማኖታዊ መሰረት የለለዉና ስለሰዉ ልጆች መላ ነጻነት ከሚሰብከዉ ሊበራሊዝም ከሚለዉ የፖለቲካ ፍልስፍና የተወሰደ ነዉ፡፡

በፕሮተሰታንት አስተምህሮ የዚህ አስተሳሰብ ዋናዉ አመንጪ ሉተር ሲሆን ከካቶሊክ ሀይማኖት በግሉ አስተሳሰብና በተቃዉሞ ሲገነጠል ‹‹መጽሃፍ ቅዱስን ማንም በገባዉ መተርጎምና መረዳት ይችላል›› የሚለዉ ጽንፈኛ አስተሳሰቡ ነዉ፡፡ በዚህ የተነሳ ከካቶሊክ የተገነጠለዉ ጨቅላዉ ፕሮተሰታንት ገና 10 አመት እንኩአን ሳይሞላዉ እንደ አመባ ማይቶሲሳዉ የሰል ብዘት ሲከፋፈልና ሲበጣጠስ ይኸዉ ዛረ ከኛ ዘመን ደርሶአል፡፡

የዚህ አስተሳሰብ እና መከፋፈል በፕሮተሰታንት ድርጅት ዉስጥ በርካታ ቀዉሶችን የፈጠረ ሲሆን ለአብነትም የሚከተሉትን እንደ መነሻ ማየት ይቻላል፡፡

1. ክርሰቶስ መድሀኒአለም (ያለም መድሀኒት) መሆኑን መጽሀፍ ቅዱስ ሲነግረን እነሱ በፖለቲካ ፍልስፍና (ሊበራሊዝም) በተቃኘ አስተሳሰባቸዉ ወደ ግል አዳኝነት ዝቅ አድርገዉታል፡፡

2. በፕሮተሰታንት አስተምህሮ ዉስጥ ያለዉ ግላዊ አስተምህሮ የእምነቱን ድርጅቶች በሙሉ ስርአት የለሽ በማድረግ ወጥ የአምልኮ ስርአት እንዳይኖር መሰረት በመሆን ተከታዮቹ የግለሰብ እምነት መሰል አስተሳሰብ ተሸካሚ እንዲሆኑ አድርጎአል፡፡

3. ይኸዉ የሊበራል አስተምህሮ በፕሮተሰታንት ዉስጥ ስርአት አልበኝነትን የፈጠረ ሲሆን ከአለባበስ ጀምሮ የአማኞቹ ህይወት ፍጹም አለማዊ እንዲሆን አድርጎአል፡፡

4. ይኸዉ የሊበራል አስተሳሰብ በፕሮተሰታንት አስተምህሮ ዉስጥ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ለግለሰቦቹ ነጻነት በመሆኑ ብዙዎቹ ከእምነቱ ባገኙት ነጻነት ወደ ግብረ ሰዶማዊነት ያመሩ ሲሆን ከዚህም ባለፈ የሰይጣኒዝም እምነት አራማጆች እንዲሆኑ አድርጎአል፡፡

5. የዚህ አስተሳሰብ ለላዉ ቁልቁለት በረጂም አመት ምእራባዉያን ጥቁሮችን በባርነት ስርአት ዉስጥ ሲያኖሩ እንደ መሰረት የተጠቀሙት የፕሮተሰታንትን እምነት ሲሆን በዚህም የሀይማኖቱ የአእምሮ ማንጠፍ ስራ የነጭ በላይነትን በጥቁሩ ላይ ተጭኖ ማንነቱን እንዲያጣ አድርጎአል፡፡

6. በሊበራሊዝም አስተምህሮ የሰከሩት የኛዉ ሀገር ምንደኞች በባንዳነት ተቀጥረዉ ተዋህዶን አርጅታለች ሲሉ ዋናዉ አላማቸዉ ለግሎባላይዘሽን መንገድን መጥረግና ሲሆን፤ ለዚህም እንቅፋት የሚሆኑትን ጥንታዊ ሀይማኖት፣ ባህል፣ እና ወግ እንዲጠፋ አጥብቀዉ መስራት ነዉ፡፡

7. እነዚህ የእምነት አሻሻጮች አጥብቀዉ የሚሰሩት ትዉልዱ ፍጹም ሊበራል እንዲሆንና ማንነቱን አራግፎ ጥሎ እንደ አፍሪካዉያን ወንድሞቻችን መሰረት አልባ እንዲሆን መጣር ነዉ፡፡

አባቶቻችን ማንነታችንን ሊያጠፋ የመጣዉን አዉሮጳዊ ሀይል በአድዋና በአምስቱ አመት ወረራ ወቅት ተዋግተዉና ድል ነስተዉ ማንነታችንን እንዳስጠበቁልን ሁሉ፤ የነሱን አሰረፍኖት ተከትለን ይኸንን የማይታይ የእምነት፣ የባህል፣ እና የማንነት ጠላት አጥብቀን ልንከላከል ያስፈልጋል፡፡

ተዋህዶ ሃይማኖታችን ደግሞ ከምንም በላይ ለሀገር አንድነት፣ ለህዝቦች እኩልነትና ነጻነት አጥብቃ የምታስተምር ሲሆን የዚህ ዉጠትም በአድዋና በአምስቱ አመት የጣሊያን ወረራ ወቅት ታይቶአል፡፡ አሁንም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ ይኽ እንቅልፍ የሚነሳቸዉ ምእራባዉያንም ትዉልዱን በራሳቸዉ ባህልና አስተሳሰብ ለማጥመቅ በመጀመሪያ ማጥፋት የሚፈልጉት ይህችን በተክርስቲያን ነዉ፡፡

የአድዋዉ ድል ለመላዉ ጥቁር ህዝብ የነጻነት ነጸብራቅ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ‹‹እኛም እንደ ኢትዮጵያ›› በማለት በ1950ወቹ እና በ1960ወቹ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ነጻ ወጥተዋል፡፡ ለዚህም መሰረቱ የአድዋዉ ያባቶቻችን ተጋድሎ ነዉ፡፡ ለዚህ ድል ደግሞ ታላቁን አስተዋጽኦ ያደረገችዉ ቅድስት በተክርስቲያናችን ናት፡፡ በተክርስቲያኒቱ ስለሰዎች ነጻነት አጥብቃ የምትሰብክ ናትና፡፡ አፍሪካን ያጡት ነጮች ለመበቀልና ለማጥፋት የሚፈልጉት ደግሞ ይህችን በተክርስቲያን ነዉ፡፡ እንደነሱ ቅዠት እሱአን አጠፉ ማለት ደግሞ ምእመናኑን በግላጭ አገኙት ማለት ነዉ፡፡

ባሁን ጊዘ ትታደስ፣ አሮጊቱአ ሳራ ወዘተ ጩኸታቸዉ መነሻዉም መድረሻዉም ይኸዉ ነዉ፡፡ በበተክርስቲያኒቱ ዉስጥ የተሰገሰጉትና በየኢንተርነቱም ሆነ በየአደባባዩ የሚጮሁት ምንደኞችም አላማቸዉ በምንደኝነት/ቅጥረኝነት የምእራባዉያንን የበተክርስቲያኒቱ ማጥፋት አላማ ማሳካት ነዉ፡፡ እንደ እባቶቻችን አኛም እምነታችንንና ሀገራችንን ከማይታይ ጠላት እንከላከል፡፡

ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር!!!!!!!”

እኔ ደግሞ የሚከተለውን ሂስ ሰጥቻለው

1. “በፕሮተሰታንት አስተምህሮ የግል አዳኝ የሚለዉ አስተሳሰብ የእምነታቸዉ መሰረት ነዉ፡፡ በእርግጥ እሱም ቢሆን እምነት ካላቸዉ ነዉ፡፡ብለሀል።

ቅር ያለኝ ነገር ቢኖር እዚህ አባባል ውስጥ በእርግጥ እሱም ቢሆን እምነት ካላቸዉ ነዉ፡፡የሚለው ነው። እኔ የምረዳው እዚህ አባባሉ ውሰጥእኔ እምነት አለኝ እናንተ ግን የላችሁምእያልክ እንደሆነ ነው፤ ከዚህም ባሻገር የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችንም የሚያንኳስስ አንድመታ እንዳለውም ይሰማኛል።

2. “ሉተር ከካቶሊክ ሀይማኖት በግሉ አስተሳሰብና በተቃዉሞ ሲገነጠል ‹‹መጽሃፍ ቅዱስን ማንም በገባዉ መተርጎምና መረዳት ይችላል›› የሚለዉ ጽንፈኛ አስተሳሰቡ ነዉ፡፡ብለሀል።

ማንም ሰው መጽሃፍ ቅዱስን በገባዉ መተርጎምና መረዳት ይችላል? ወይም አይችልም? የሚለውን ንትርክ ለግዜው ወደጎን እናድርገው እና ስለ ሉተር ( የፕሮቴስታንት እምነት መስራች) ያለውን ለማየት ልሞክር።

ሉተር ‹‹መጽሃፍ ቅዱስን ማንም በገባዉ መተርጎምና መረዳት ይችላል›› ብሎ በማመኑ እና በማለቱ ፅንፈኛስትል (ዮናስ) ፈርጀሀዋል። ፅንፈኛ ምን ማለት ነው? ኢህአዴግም አክራሪና ፅንፈኛ የሚሉትን ቃላት አንዱን ባንዱ እየተካ ሲጠቀምበትም አስተውያለሁ።
አኔ ሲገባኝ አክራሪ ማለት እምነቱን አጥብቆ የሚይዝ እና በእምነቱ የማይደራደር ሲሆን ፅንፈኛ የሚለው ደግሞ እምነቱን አጥብቆ የሚይዝ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ነገር ግን ከራሱ እምነት አልፎ ተርፎ በሰዎች እምነት ጣልቃ እየገባ የሚፈተፍት፣ የሚያጥላላ፣ የኔ እምነት ትክክል ነው የናንት ስህተት ነው፣ እኔ እምላችሁን ስሙ እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነም እርምጃ ሊወስድ የሚችል የአስተሳሰብ ፅንፍ ነው። ታድያ ሉተር ‹‹መጽሃፍ ቅዱስን ማንም በገባዉ መተርጎምና መረዳት ይችላል›› በማለቱ እንዴት ፅንፈኛ አስተሳሰብልትለው ቻልክ? በእርግጥ ሉተር ከዚህም በላይ በመፅሀፍ ቅዱስ ውሰጥ የማይስማማባቸውን አንቀፆችን ለይቶ በማውጣት እንደማይስማማባቸው በይፋ ከመናገሩም በላይ ከቤተ ክርስቲያኗ በራፍ ሰው እንዲያነበው ለጥፎታል፤ በዚህም ውድ ህይወቱንም ከፍሏል። ዮናስ ሆይ የሞትን ፅዋ በ16ኛው ክ/ዘመን ለተጎነጨ ሰው ፅንፈኛ ብትለው ብርቁ አይሆንም። ማርቲን ሉተር የስነ እምነት ፕሮፌሰር (theology) እንደነበሩም የረሳህ ይመስለኛል።

3. ዮናስ በተራ ቁጥር 1 ላይ ያለውን ስመለከት…(በሊበራሊዝም) በተቃኘ አስተሳሰባቸዉ…” የሚል ነገር አለ።
ከዚህ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ደሞ በፕሮቴስታንት ላይ ያነጣጠረ ጭፍን ጥላቻ ነው። ዮናስ አንተ ክርስቶስ የዓለም መድሀኒት ነው ብለህ ታምናለህ፣ እነሱ ደሞ የግል አዳኝ ነው ብለው የሚያምኑ ከሆነ መብታቸው ነው። አንተ እንዳገርህ ቀድስ እነሱም እንዳገራቸው ይቀድሱ። ለዚህ ማጠናከሪያ ይሆኖ ዘነድ ኢህአዴግ የሚላት አንድ አባባል ልዋስ ፍቀድልኝ ልዩነታችን ውበታችን

4. አሁንም ከተራ 1 ቁጥር ሳንወጣየእምነቱን ድርጅቶች በሙሉ ስርአት የለሽ…” ብለህ ትላለህ። ስርዓት የለሽማለት ግልፅ የሆነ ስድብ ነው፤ ከስድብም በላይ ፅንፈኛነት ነው። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ፅንፈኛ ማለት ከራሱ እምነት አልፎ ከሌሎች እምነት ውስጥ ገብቶ የሚፈተፍት፣ የሚሳደብ የሚያንኳስስ ወዘተ. ማለት ከሆነዮናስ ሆይ ሉተር ሳይሆን ፅንፈኛው አንተ ነህ።

5. በተራ ቁጥር 3 ደግሞ እንዲህ ይላልከአለባበስ ጀምሮ የአማኞቹ ህይወት ፍጹም አለማዊ እንዲሆን አድርጎአል።

ውድ ዮናስ ማንም ሰው በዚች አለም እንደ አለማዊ ወይም ደግሞ እንደ መንፈሳዊ የመኖር መብቱ እስከሆነ ድረስ እባክህን ይኑርበት አትረብሸው እልሃለው።

ከአለባበስ አንፃር የተናገርከው ደሞ ምንም እንኳ መፅሀፍ ቅዱስ እና ቁርአን የአለባበስ ስርአት ያስቀመጡ ቢሆንም የእምነቶቹ ተከታዮች እምብዛም ለአለባበስ ስርአቱ ሲገዙ አይስተዋልም፤ አለመገዛትም መብታቸው መሆኑን አትረሳ። ልታስገድዳቸውም አትችልም። ምናልባት አንተ የሴት ልብስ ትለብሳለህ ብየ ባልገምትም እህትህና እናትህ የወንድ ሱሪ አለመልበሳቸውን ልብ በል ምክኒያቱም ትገስፃቸው ዘንድ ቅርቦችህ ናቸውና። (የራሷን ሳታይ…..)

6. በተራ ቁጥር 4٫ከእምነቱ ባገኙት ነጻነት ወደ ግብረ ሰዶማዊነት ያመሩ ሲሆን ከዚህም ባለፈ የሰይጣኒዝም እምነት አራማጆች እንዲሆኑ አድርጎአል፡፡ላልከው ደግሞ ማንኛውም የእምነት ነፃነት ሰዶማዊነትን ና የሰይጣኒዝምን እምነት ያራምዱ ዘንድ አይጋብዝም። አይ….. ካልክ እንዳገርህ ቀድስ ነገር ግን ምላስክን ሰብስብላቸው።

  1. 7. በተራ ቁጥር 5٫…. የነጭ በላይነትን በጥቁሩ ላይ ተጭኖ ማንነቱን እንዲያጣ..” ለምትለው ነገር እኔ በፕሮተሰታንት እምነት ውሰጥ ብዙም አይታየኝም ምክኒያቱም ስእለ አድህኖ ስለማይጠቀሙ። በአብዛኛው ነጭ የመላእክት ጥቁር የአጋንንት ተደርጎ የሚሰራው ስእል አስተውለህ ከሆነ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ነጭ ቀለም እንዲኖራቸው ተደርገው ይሳላሉ። እስቲ ነጭ ኢትዮጵያዊ አለ ? አለ ካልክ አሁንም መብትህ ነው። እንዳገርህ ቀድስ! ቅር ያለኝ ነገር እነ ቫለንታይን እነ የውሀ ቀን እነ ፍሪደም ዳቦ ቤት እነ የጎንደር እስክስታ በአትላንታ ክለብ ለምን አልታዩህም እሳ?

8. “….ምንደኞች በባንዳነት ተቀጥረዉ …. የእምነት አሻሻጮች እንደ አፍሪካዉያን ወንድሞቻችን መሰረት አልባ እንዲሆንወዘተ. ” ላልካቸው ምንም ማለት አልፈልግም ምክኒያቱም ቁልጭ ያሉ የአንተን ፅንፈኛነትን የሚያሳዩ ናቸው።

“…እንደ አፍሪካዉያን ወንድሞቻችን መሰረት አልባ እንዲሆን…” አፍሪካውያን መሰረት አልባ ናቸው እንዴ?

ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር“……… ላልከው ትኑርልህ ለኔ ደሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑርልን!!!

ሰው፦ ሰው ስለሆነ ብቻ ሊከበር ይገባዋል፤ አስተሳሰቡ እና እምነቱም እንዲሁ። ነገር ግን አስተሳሰቡን እና እምነቱን መከተል ሌላ ጉዳይ ነው። ምክኒያቱም ማክበርና መከተል አንድ አይደሉምና።


ቢላል አዱኛ
አዲስ አባባ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s