ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ተደበደበ

በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖረው ተወዳጁ ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ባልታወቁ ሰዎች በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ጉዳት ደርሶበታል። በትላንትናው እለት ሊመሽ አካባቢ በዲሲ ሰዓት አቆጣጠር 5፡15pm ላይ ጆርጂያና ኬኔዲ መንገድ ጥቂት እርምጃ ገባ ብሎ በተፈፀመበት ድብደባ በግራ ቅንድቡ ከፍ ብሎ በድብደባ ክፉኛ በማበጡ የግራ አይኑን እብጠቱ የሸፈነው ሲሆን በግንባሩ አካባቢ ተሰንጥቆ ደም ይፈስ ነበር። በመሃል አናቱም ተመሳሳይ ደም ይፈስ የነበረ ሲሆን መላ አካሉ በደም ተነክሮ ነበር። በጉሮሮው አካባቢ የመታነቅ ሁኔታ እንደገጠመው ሲታይ በጣም የተጎዳው ፋሲል ሚዝኑን ጠብቆ ለመቆም ሲቸገር ተስተውሏል። ደም ወደ ጭንቅላቱ ውስጥ እንዳይፈስ አንዳንዶች ሰግተዋል። በአጋጣሚ በአካባቢው የነበሩት ድምፃዊ ግዛቸውና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደንግጠው ሲጯጯሁና ሲላቀሱ ፋሲልን የከበቡት 5 ፖሊሶች እንዲረጋጉ በመጠየቅ የተጐዳው ፋሲል በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርገዋል። ድምፃዊውን ማን ደበደበው?

by .Aesegd Tamene

Advertisements

ስለ ሜሮን ጌትነት ግጥምና ውዝግቡ -አትሂድ

ቁም ነገር መፅሔት ቁጥር 193 ታህሣስ 2007
ለሶደሬ

መቼም ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ህዝቡ እየተቀባበለው ያለውን ‹አትሂድ› የሚለውን የሜሮን ጌትነት ግጥም አልሰማሁም አትለኝም? ወር በገባ በመጀመሪያው ረቡዕ በራስ ሆቴል በሚቀርበው የግጥም ምሽት ላይ ያቀረበችው ግጥም የመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎችን የጦፈ ውዝግብ ውስጥ ከቷቸዋል አሉ፡፡
እናስ? እናማ አንዳንዶች ግጥሙ የሜሮን አይደለም፤ ሜሮን የሌላ ሰው ግጥም ነው ያነበበችው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ግጥሙ የራሷ ነው ለዚሁም ማስረጃ የሚሆነው ከሳምንት በፊት ሜሮን ራሷ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መ/ቤት ባለስልጣን ቢሮአቸው ድረስ አስጠርተዋት‹በእርግጥ ይህ ግጥም ያንቺ ነው? › ብለው ጠይቀዋታል አሉ፡፡
እናስ? እናማ ግጥሙ የራሷ እንደሆነ ስትገልፅላቸው በግጥሟ ውስጥ የጠቀሰቻቸው ሀሳቦች በግልፅ ከመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የሚላተሙ እንደሆኑ በመግለፅ በቅርቡ በሚዘጋጅላት አንድ የሬዲዮ ጣቢያ/ዛሚ?/ ላይ ለቃለ ምልልስ ላይ ቀርባ እንድታስተባብል ጠይቀዋታል አሉ፡፡ እናስ? እናማ ሜሮንዬ ‹ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ!› ከሬዲዮ ጣቢያው በተደጋጋሚ ቢደወልም የሜሮን ስልክ ዝግ ሆኖ ይከርማል፡፡
በዚህ መሀል የህዳር 29 የብሔር ብሔረበሰቦች ቀን ሊከበር ነው ሲባል የህዳሴው ግድብ ከሚሰራበት ቤንሻል ጉል ክልል አሶሳ ስታዲየም በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሚገኙበት ሲከበር ‹መድረኩን ማን ይምራ?› የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ አስቀድመው በጀት አስመድበው በዓሉን ለማክበር ወዲያ ወዲህ ከሚሉት አርቲስቶች ጋር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ጋር ስብሰባ ይቀመጣሉ አሉ፡፡
እናስ? እናማ የዕለቱን መድረክ ማን ይምራ ሲባል ‹ሜሮን› የሚል ስም ይነሳል፡፡ ዋንጫውን ከክልል ክልል ይዘው በማስጎብኘት ላይ ካሉት አርቲስቶች መሀከል ሁለቱ የሜሮንን ኢ ልማታዊ ግጥም በመጥቀስ ‹መንግስትን በግልፅ እየተቸች እንዴት?‹ ብለው ሽንጣቸውን ገትረው መቃወም ይጀምራሉ አሉ፡፡ እኛ ከመንግስት ጋር በመስራታችን ውግዘት እየደረሰብን እንዴት በግልፅ የሚቃወሙትን መድረክ ላይ እናወጣለንም ብለዋል አሉ፡፡
እናስ? ዳኛው የፌዴሬሽ ምክር ቤት አፈ ጉባኤው ምን ቢሉ ጥሩ ነው? በሜሮን ግጥም የተነሳ ዲያስፖራው ከፍተኛ መነቃቃት ላይ በመሆኑ ይህንን መነቃቃት ላይ ውሃ መቸለስ የምንችለው ሜሮንን ስናሰራት ብቻ ነው አሉ ተባለ፡፡ እናም የሜሮን ስልክ ለዚህ በዓል እንደተፈለገ ሲያውቅ በራሱ ጊዜ ተከፈተ አሉ እና ወደዚያው አመራች፡፡›
የአምስት ወር ነፍሰ ጡር የሆነችው ሜሮን በሬዲዮ የግጥሙን መልዕክት ‹አስተባብይ› በተባለች ማግስት ወደ እጮኛዋ ጋር አሜሪካ ሄዳ ልጇን ለመገላገል ትኬት መቁረጧ ሲታወቅ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘወትር እሁድ ከሚቀርበው ዳና ድራማና ዘወትር ሐሙስ ከሚተላለፈው የኢቲቪ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ላይ ትገለላለች ተብሏል፡፡ በተለይም ከዳና ድራማ ላይ ዋና ገፀባህሪ ሆና ከመጫወቷ አንፃር ድራማው ክፍተት ሊኖረው እንደሚችል የተሰጋ ቢሆንም በድራማው ላይም ነፍሰጡር መሆኗን መነሻ በማድረግ በድራማው ላይ ከደረሰባት አደጋ ጋር በተያያዘ ‹ለህክምና ወደ ውጪ ሀገር ሄደች› በሚል ታሪክን ለማስቀጠል እየተሞከረ እንደሆነ ይወራል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ አሜሪካ የምትሄደው ሜሮን ‹አትሂድ› በሚለው ስደትን በሚሰብከው ግምሟ እንዲህ ትላለች..
አትሂድ አትሂድ ብዬህ ጮኬ ነበር ብዕሬን አንስቼ
የሀገርን ጥቅም የወገንን ፍቅር በአክብሮት አይቼ
እዚህ ለፍተህ ስትኖር በሀገርህ አፈር ላይ
በርታ ጎብዝ የሚል ያንተን ልፋት የሚያይ
አንዳችም ሰው የለ
ህዝቡ ውጪ አምልኳ ልቡ ተንበርክኳል
ለሀገር ስታነባ በጥቅም ይለካል
በነፃ ያላበህ በዶላር ይለካል… ብል ቻዎ…

https://www.youtube.com/watch?v=LbzCwEKfKaY

አቶ ሽመልስ ከማል ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።

የአቶ ሽመልስን ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

አቶ ሽመልስ በቅርቡ የታዩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው በድርጅቱ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው፡፡ የፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ ከአቅም ማነስና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ተያይዞ በድርጅቱ ጋዜጠኞች እየቀረበባቸው ያለውን ግልጽ ትችትና ቅሬታ በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከማስተባበላቸውም በተጨማሪ ጥያቄውን የሚያነሱ ጋዜጠኞችን እስከማስፈራራት የደረሰ ንግግር ሲያደርጉ የተሰሙት አቶ ሽመልስ፣ መደበኛ ስራቸውን መተዋቸው በኮምኒኬሽን መ/ቤቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖአል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ በረከት ስምኦን ደጋፊነት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ስራአኪያጅ የነበሩ ሲሆን፣ የ97 ምርጫን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተከሰሱ ወቅት አቃቤ ሕግን ወክለው ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲቀርቡና ሐሰተኛ ምስክሮችን በገንዘብ በመግዛትና በመደለል ለኢህአዴግ ውለታ ለመስራት የጣሩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ አቶ በረከት ከጤና ጋር በተያያዘ ስራቸውን እየተዉ በመምጣታቸው አቶ ሽመልስ ብቸኛው ደጋፊያቸውን አጥተዋል። አቶ ሽመልስ አቶ በረከትን የመተካት ህልም ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው አቶ ሬድዋን ቦታውን እንዲወስዱ ተደርጓል። በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ፣ አቶ ሽመልስ ከስራቸው የሚባረሩበት ቀን እሩቅ ላይሆን እንደሚችል ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን በመልቀቅ ከአገር ለመውጣት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስ የስልጣን ቆይታ በከፍተኛ ህመም ከሚሰቃዩት ከአቶ በረከት ስምኦን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

አሰግድ ታመነ

ኢትዮጵያዊት እናት

እናቴ አንድ እይን ብቻ ነው ያላት በዛም የመጣ በጣም እጠላታለው:: አባቴ…አባቴ ደሞ የአራስ ቤት ልጅ እያለው ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኋላ እኔና እናቴ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነትጋ መኖር ጀመርን:: አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ
እናቴ በራችንጋ ትንሽዬ ሱቅ ከፍታ መስራት ጀመረች እማ ለኔ የማታደርግልኝ ነገር የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር ትዝ ይለኛል 5ኛ ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ ትምህርት ቤት አበባ ይዛልኝ መጣች “እንዴት እንዲ ታደርገኛለች? ማን ነይልኝ አላት?” ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን ገልምጫት እየሮጥኩ አዳራሹን ለቅቄ ወጣው::

በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ” እናቱ 1 አይን ነው ያላት” እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚች አለም ብጠፋ ብዬ ተመኘው እቤት ስደርስም” ደስ ይበልሽ በጓደኞቼ አሳቅሽብኝ….ቆይ እንድ አይንሽ የት ሄዶነው? ሁሌ እንዲ ከምታሸማቂኝ ለምን አትሞቺም?” ብዬ ጮህኩባት ምንም መልስ ሳትሰጠኝ ወጣች:: እንዲ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴ ውስጤን ቀለል አለኝ ብዙም ስሜትዋን የጎዳሁት አልመሰለኝም ነበር ያን ቀን ማታ ከእንቅሌፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ እቃ ቤትስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ቅስ ብላ
ስታለቅስ አገኘዋት ቅድም ባልኳት ነገር እንደሆነ ገባኝ::

አሳዘነችኝ!
ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ካንዱ አይንዋየሚወርዱ እንባዎቿን እየዋቸው:: አይንዋ በእንባ ተሞልቶ ሳየው ይበልጥኑ ጠላኋት! በዛው ቅፅበት ለራሴ እንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ ስኬታማ ስሆን እንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት
እንደምሄድ!

ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ እናቴን ትቻት ወደ ከተማ በመሄድ አለ በሚባል ዩንቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ ጥሩ ስራ ያዝኩ፤ የራሴን ቪላ ገዛው ሚስት
አግብቼምልጆች ወለድኩ:: አሁን የተመኘሁትን የልጅነት ህይወት እየኖርኩ እገኛለው:: በጣም ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ አለኝ፤ ቆንጆ ቤት አለኝ፤ ደስተኛ ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ ነውና የምኖረው ደስተኛ ነኝ::

አንድ ቀን ግን ያላሰብኩት ዱብ እዳ መጣብኝ “ምን?!
ማነው ?!” እናቴ ነበረች ፀጉሮችዋ ሸብተው ከስታና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶች ለብሳ መጣች ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው?! ህፃንዋ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደቤት ገባች
እንዳላወቀ በመምሰል “ሴትዮ ምን ፈልገሽ ነው?
የሰው ቤት ዝም ተብሎ እይገባም እሺ ውጪልኝ
ከቤቴ!!” አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች” ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው” ብላኝ ወጣች …..ተመስገን አላወቀችኝም::

ይህ ከሆን ካንድ ወር በኋላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የት/ ቤቱ ዳይሬክተር ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ ፕሮግራሙ ሲያልቅ በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ አገኘዋት:: ሞታለች!! ምንም አላላቀስኩም:: እጇ ላይ ወረቀት አየውና አንስቼ
ማንበብ ጀመርኩ ለኔ የፃፈችው ደብዳቤ ነበር…እንዲህ ይላል

“ውድ ልጄ, ካሁን በኋላ ሕይወት ማለት ለኔ ምንም
አይደለችም:: እንተ ወደ ምትኖርበት ከተማም ተመልሼ አልመጣም:: ልጄ ከምንም በላይ ግን ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው ለምን አንድ አይን ብቻ እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር እውነታው ይህ ነው ልጄ …..ልጅ እያለክ ከባድ የመኪና አደጋ ይደርስብክና አንድ አይንክ ይጠፋል እንደማንኛውም እናት ያለ አንድ አይን ስታድግ ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንት እንዲያረጉልህ ዶክተሮቹን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው አደረጉልህ….. ለዚ ነው እንድ አይናማ የሆንኩብክ:: እይዞህ ልጄ ባደረካቸው ነገሮች ተቀይሜህ አላውቅም ነበር
ባለፈው እቤትክ መጥቼ የልጄን ልጅ በማየቴ በጣም ተደስቻለው:: ለወደፊትም በደስታ እንደምትኖርም ተስፋ አደርጋለው:: ልጄ እናትህ በጣም ትወድሃለች”

የዛሬ የሐና ጉዳይ የፍርድ ቤት ውሎ እንዲህ ይመስል ነበር

በአዜብ ወርቁ ተፃፈ
ስለዛሬው ቀጠሮ ጉዳይ ለመነጋገር ለሐና ቤተሰቦች ትላንት ማታ ስንደውል ባለፈው ከጠዋቱ በ12 ሰዓት በዝግ ችሎት መታየቱን በማስታወስ ነገ ከሌሊቱ 12 ሰዓት ለመሄድ ወስነናል አሉን እና ተቀጣጠርን እኛ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ስንደርስ እነሱ ከሌሊት 11 ሰዓት ደርሰው ሲጠባበቁ አገኘናቸው፡፡ 11 ሰዓት ላይ የፍርድቤቱን በር ሲያንኳኩ ጥበቃው መቼ ነጋ? ፍርድቤት በሌሊት መስራት ጀመረ እንዴ ብሎ ተደናገጠ አሉ፡፡ እኛም ባለፈው ይሄን ጥያቄ ጠይቀን ነበር ግን በሌሊት በ12 ሰዓት ማየት ጀምረናል ሲሉ እንግዲህ ቢጀምሩ ነው ብለን አምነናቸው ነው ፡፡ በሌሊት መጥተን ፍርድ ቤቱ እስኪከፈት እስከ 3 ሰዓት ድረስ በር ላይ ቆመን ስንጠባበቅ ቆየንና በሩ ወለል ብሎ ለባለጉዳዮች ሲከፈት ገባን እስከ 4 ሰዓት ድረስ ተጠባበቅን መረጃ ጠያየቅን እዚህ ሳይሆን ልደታ ፍርድቤት ተዘዋውሯል እዚህ አይቀርብም የሚል ነገር ሰማንና ሁለት ሆነን ሌሎቹን እዛ ትተን ልደታ ለማጣራት ሄድን ልደታ እነሱ ጋ እንዳልደረሰ እና ሜክሲኮ የሚገኘው አንደኛ ፍርድቤት እንደሆነ ተነገረን ተመለስን ሜክሲኮ ፍርድቤት ደግሞ በተያዘለት ቀጠሮ መሰረት በዕለቱ እዛው እንደሚቀርቡ ግን ወደ ረፈዱ ላይ እንደሚሆን ተነገረ ተባለ እና ተበታተንን ፡፡

በመጨረሻም 10 ሰዓት ላይ ቀረቡ እና ምርመራው ስለተጠናቀቀ ወደ ከፍተኛ ፍርድቤት እንደተላለፈ እና ዕሮብ ታህሳስ 8 ከፍተኛው ፍርድቤት እንደሚቀርቡ ሰማን
ደስ ይላል የምርመራ መዝገቡ ተጠናቆ ወደ ከፍተኛ ፍርድቤት መተላለፉ ትልቅ ነገር ነው፡፡
ነገር ግን አንድ መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ አለ
ለምንድነው ተጠርጣሪዎቹ ፍርድቤት የሚቀርቡበት ሰዓት እና ጉዳዩ ሚስጢር እንዲሆን የተፈለገው?
ግርግር እንዳይፈጠር ጸጥታ እንዳይደፈርስ ነው የሚባል ነገር ሰምቻለሁ በማን ?
እንዴ ፍርድ ቤት ተገኝታችሁ እኮ ብትመለከቱ ባለፈው ከቅርብ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶች ውጪ ከለቤተሰቦቿ አይዞአችሁ አብረናችሁ ነን ለማለት እና በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር ማዘናችንን ለማሳየት የተገኘነው ሰዎች 10 ብንሆን ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ጠዋት ከቤተሰቦቿ ውጪ የነበርነው 3 ነበርን ለዘውም ተከፋፍለን አንዳችን ጠዋት ሁለቱ ከሰዓት እንዴት ነው ግርግር እና ጭንቅንቅ የታየው?
ለምንድነው የሐና ቤተሰቦች በልጃቸው መጎዳታቸው ሳያንሳቸው እንደገና ፍትሕ ፍለጋ የሚጉላሉት?
ከሰዓት 10 ሰዓት ላይ ለሚቀርብ የምርመራ መዝገብ እነሱ ከ ሌሊቱ 11 ሰዓት የፍርድቤት በር ማንኳኳት እና በዛ ውርጭ በሩን የሙጥኝ ብለው መጠበቅ ትክክለኛውን ጉዳዩ የት እንደሚታይ የሚናገር መረጃ የሚሰጥ ጠፍቶ አንዱ ፒያሳ አንዱ ልደታ አንዱ ሜክሲኮ መንከራተት ለምን አስፈለገ?
እረ ለተጎጂ ቤተሰቦች አክብሮት እና እንክብካቤ በመስጠት ከልብ መቆርቆራችንን እና ሐዘኔታችንን እናሳይ
ፍትሕ ለሐና!

ሽመልስ ከማልና ፈትያ የሱፍ በፕሬስ ድርጅት እየተወዛገቡ ነው

‹ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱ ለበላይ አካል እናሳውቃለን›› ፈትያ የሱፍ
‹‹ችግሮቹ ውጫዊ ናቸው›› አቶ ሽመልስ ከማል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዙሪያ እየተወዛገቡ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል የፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ላለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በተለያዩ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ በቦርድ ሰብሳቢነታቸው ችግሮቹን መፍታት የነበረባቸው ቢሆንም ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ችላ በማለት ድርጅቱ ከእነ ችግሮቹ እንዲዘልቅ አድርገዋል በማለት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን የ2007 የበጀት እቅድን ለመገምገም በተገናኙበት ወቅት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር በበርካታ ችግሮች ዙሪያ ወቀሳ እንደደረሰበትና ችግሮቹ እንዲፈቱም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ በራሱ ድርጅት እየታተመ የሚወጣው ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ አስነብቧል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር ብልሹነት መኖሩን የተናገሩት ፈትያ የሱፍ፣ ‹‹በራሱ ድርጅት በችግር የተተበተበ ጋዜጠኛ እንደምን የሌሎችን ድርጅቶችና ግለሰቦች የአሰራር ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም በተደጋጋሚ ችግሮቹ ለድርጅቱ አስተዳደር በሰራተኞች ሲቀርቡለት የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ማለፉን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አውስተዋል፡፡

ፈትያ የሱፍ እንደሚሉት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር ችግሮቹን በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ ወደሚመለከተው ከፍተኛ አካል ለማስተላለፍ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው የድርጅቱ ችግሮች ውጫዊ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ድርጅቱ የበጀት ችግሮች እንዳለበት ያወሱት አቶ ሽመልስ፣ በተጨማሪ ግን በድርጅቱ ላይ መጥፎ እይታ ያላቸው እና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት በሰራተኞች ስም አላማቸውን ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ወገኖች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹የግል እና የመንግስት ሚዲያ ይለያያሉ፤ በአመለካከት፣ በአሰራርና በጥራት ልዩነት አላቸው›› በማለትም ሰራተኞቹ ፕሬስ ድርጅት እንደ ግል ሚዲያ ሊሰራ እንደማይችል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ እና አቶ ሽመልስ ከማል ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስሮሽ እንዳላቸው የሚገልጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በዚህ ትስስራቸው የተነሳም የአቶ ሽመልስ ከማል ባለቤት ያለምንም ውድድር በድርጅቱ በጋዜጠኝነት ተቀጥራ ምንም ስራ ሳትሰራ ደመወዝ ትወስድ እንደነበር፣ በኋላ ግን ‹ስራውን አልቻልኩትም› በሚል ከድርጅቱ እንደወረጣች ይናገራሉ፡፡

አቶ ሰብስቤ ከበደ በሰራተኞች ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው እና በተለያዩ ስብሰባዎች በይፋ ‹አልቻልክም ድርጅቱን ልቀቅ› ተብለው በሰራተኞች እንደተነገራቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር ባለቸው የጥቅም ትስስር በስልጣናቸው እስካሁን እንደሚገኙ፣ ይህም ድርጅቱን እና ሰራተኞችን እየጎዳ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

posted by Aseged Tamene